6ኛው የአፍሪካ ዋና ኦዲተሮች ማህበር የአካባቢ ኦዲት የሥራ ቡድን (AFROSAI- WGEA) “በአፍሪካ ውስጥ ጤናማና ዘላቂ አካባቢ እንዲኖር በጋራ እንስራ” በሚል ርዕስ ከመስከረም 2 – 6/2009 ዓ.ም አቡጃ ናይጄሪያ ላይ ተካሂዷል፡፡ በስብሰባው ላይ የፌዴራል ዋና ኦዲተር ክቡር አቶ ገመቹ ዱቢሶ በሚመራ ልኡካን ተሳትፎ አድርጓል፡፡ በሰብሰባው ላይም የዘላቂ የልማት ግቦች እና የዋና አዲተር መ/ቤቶች ሚና፣ በአባል አገሮች መካከል ስለሚከናወኑ የተለያዩ የትብብር ኦዲቶች እና የፕላስቲክ ምርት ውጤቶች በአፍሪካ ውስጥ እያደረሱ ያሉት የአካባቢ ብክለቶች እና በአህጉራችን ያሉ ምርጥ ተሞክሮዎች የሚሉት ዋና ዋና የመወያያ ርዕስ ጉዳዮች ነበሩ፡፡ በተጨማሪም አካባቢ ጥበቃን በተመለከተ በአስተናጋጇ አገር በአቡጃ በተግባር እየተከናወኑ ካሉ ሥራዎች ውስጥ በተወሰኑ ሥፍራዎች የመስክ ጉብኝት ተደርጓል፡፡
6ኛው የአፍሪካ ዋና ኦዲተሮች ማህበር የአካባቢ ኦዲት የሥራ ቡድን (AFROSAI- WGEA)
