የመ/ቤቱ ሰራተኞች 9ኛውን ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን አከበሩ
የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ሰራተኞች 9ኛውን ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን “ሰንደቅ ዓላማችን የሉአላዊነታችን መገለጫ፤ በብዝሀነት ላይ ለተመሰረተው አንድነታችን አርማ ነው! በሚል መሪ ቃል ጥቅምት 7 ቀን 2009 ዓ.ም በተቋሙ ቅጥር ግቢ ከኢ.ፌ.ዴ.ሪ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴርና ከኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ሰራተኞች ጋር በጋራ አከበሩ፡፡
በስነ-ስርዐቱ ላይ የመስሪያ ቤቱ ሰራተኞች የኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝሙርን በመዘመር ሰንደቅ አላማውን በክብር የሰቀሉ ሲሆን ለበአሉ የተዘጋጀውን ቃለ መኃላ በጋራ በማንበብ ለተፈጻሚነቱ በሰንደቅ አላማው ፊት ቃል ገብተዋል፡፡
የዘጠነኛው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በዓል ቃለ መኃላ
እኛ ኢትዮጵያውያን የድህነትና ኋላቀርነት ታሪክ ከሀገራችን ተወግዶ፣ ኢትዮጵያችን በልማትና በዴሞክራሲ ጎዳና በፍጥነት ተራምዳ ሩቅ በማይባል ጊዜ ውስጥ መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገሮች ተርታ ትሰለፍ ዘንድ የጀመርነውን የኢትዮጵያ ህዳሴ ወደ ማይቀለበስ ደረጃ እንዲደርስ፤ ሁለንተናዊ መዋቅራዊ ለውጥ በማረጋገጥ ሂደት ላይ የሚታዩ የመልካም አስተዳደርና የኪራይ ሰብሳቢነት አደጋዎችን በማስወገድ ሁለተኛውን የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዳችንን ለማሳካት በሀገራችን ሰንደቅ ዓላማ ፊት ቃል እንገባለን፡፡