የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ዋና ኦዲተር መ/ቤት የስራ ሀላፊዎች ጥቅምት 4/2014 ዓ.ም በፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት በመገኘት የልምድ ልውውጥ አካሄዱ፡፡
የክልሉ ዋና ኦዲተር መ/ቤት የስራ ሀላፊዎች በፋይናንሻልና ክዋኔ ኦዲት ስራዎች አፈጻጸም፣ በኦዲት ጥራት ማረጋገጥ ስራ፣ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ልማትና አጠቃቀም፣ በትምህርትና ስልጠና፣ በህዝብ ግንኙነት፣ እንዲሁም ከበጀት፣ ከድርጅታዊ መዋቀር፣ ከዕቅድ አፈጻጸም፣ ክትትልና ግምገማ ስራዎች ወዘተ. ጋር በተገናኙ ጉዳዮች ረገድ በፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት በኩል እየተሰሩ ስላሉ ተግባራት ጉዳዩ በሚመለከታቸው ዳይሬክተሮች ገለጻ ተደርጎላቸዋል፡፡ የክልሉ ዋና ኦዲተር መ/ቤት የስራ ሀላፊዎችም በበኩላቸው በመ/ቤታቸው በኩል እየተሰሩ ስላሉ ስራዎች ገለጻ አድርገዋል፡፡
በልምድ ልውውጥ መድረኩ ላይ በቀጣይ በጋራ መስራት በሚቻልባቸው መስኮች ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡