መ/ቤቱ በፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የማዕከላዊ ወኪል ሥር ለሚገኙ ሠራተኞች የመቤቱን የአስተዳደርና የህግ ማዕቀፎች በተመለከተ ስልጠና ሰጠ፡፡
ከጥቅምት 5 እስከ ጥቅምት 6/2017 ዓ.ም በመ/ቤቱ የሥልጠና ማዕከል የተሰጠው የሁለት ቀናት ስልጠና የፌዴራል መንግስት ሰራተኞች አዋጅ፣ የዋና ኦዲተር መ/ቤት የሰራተኞች አስተዳደር ደንብ እንዲሁም የዲሲፕሊን አፈፃፀምና የቅሬታ አቀራረብ ስነ-ስርዓት ደንብ ላይ ያተኮረ መሆኑ ከመ/ቤቱ የትምህርትና ሥልጠና ዳይሬክቶሬት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
የስልጠናው ዓላማም በዋናነት ሰራተኞች ሥራቸውን ሲያከናውኑ መብትና ግዴታቸውን አውቀው በህግ አግባብ እንዲሰሩ አቅም ለመፍጠር መሆኑን ተገልጿል፡፡
የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የውስጥ አቅምን ተጠቅሞ የሰራተኛውን አቅም ለማጎልበት የተለያዩ ስልጠናዎች እየሰጠ የሚገኝ ሲሆን በቀጣይም ለሁሉም ወኪል መ/ቤቶች መሰል ስልጠናዎች እንደሚሰጡ ታውቋል፡፡