The International Organization of Supreme Audit Institutions (INTOSAI) Working Group on Environmental Auditing (WGEA) has confirmed that the Ethiopian Office of the Federal Auditor General (OFAG-Ethiopia) is actively operating the Environmental Auditing.
In the global survey of the international organization, launched in September/2024, the Ethiopian Office of the Federal Auditor General (OFAG) is found to be significantly active in Environmental Auditing.
The highlight of the finding & the link of the entire survey are attached for extensive reading.
የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የኦዲት ተደራሽነት አለም አቀፋዊ እይታ
የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ከሚያከናውናቸው የኦዲት አይነቶች መካከል የአካባቢ ጥበቃ ኦዲት (Environmental Audit) አንዱ ነው፡፡
ይህ ኦዲት በአካባቢ ጥበቃ ላይ መሠረት ያደረጉ የተለያዩ ኦዲቶችን የሚያደርግ ሲሆን በአለም አቀፉ የዋና ኦዲት ተቋማት ማህበር (The International Organization of Supreme Audit Institutions -INTOSAI) ስር በሚገኘውና የተለያዩ የአለም ሀገራት የኦዲት ዋና ተቋማት በአካባቢ ኦዲት ላይ እያደረጉ ያሉትን እንቅስቃሴ፣ አካሄድና ውጤት በሚመለከት ጥናት በማድረግ ጠቃሚና ልምድ የሚቀሰምባቸው የጥናት ውጤቶችን የሚያቀርበው የአለም አቀፉ የዋና ኦዲት ተቋማት ማህበር የአካባቢ ኦዲት ስራዎች ግሩፕ (The INTOSAI Working Group on Environmental Auditing -WGEA) ባለፉት ጊዜያት በአለም አቀፍ ደረጃ መረጃን በማሰባሰብ የተለያዩ ሀገራትን የዋና ኦዲተር ተቋማት የአካባቢ ኦዲት ትግበራና እንቅስቃሴ በሚመለከት ያካሄደውን አለም አቀፍ ጥናት ውጤት በቅርቡ እ.አ.አ በመስከረም 2024 ይፋ አድርጓል፡፡
በዚህ የጥናት ሰነድ የተቀመጠውን የኢትዮጵያን የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የአካባቢ ኦዲት እንቅስቃሴ የሚመለከት የጥናት ውጤት አጭር መረጃ ቀጥሎ የቀረበ ሲሆን ሙሉ መረጃ ለሚፈልጉም የጥናት ሰነዱ ሊንክ በመጫን ማግኘት ይቻላል፡፡