የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ለጋምቤላ ክልል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ኦዲተሮች በክዋኔና በነጠላ ኦዲት አሰራሮች ላይ ያተኮረ የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ፡፡
ከታህሳስ 22-28 ቀን 2017 ዓ.ም ለ 5 ተከታታይ ቀናት በጋምቤላ ከተማ በተሰጠው ስልጠና የክዋኔና የነጠላ ኦዲት ምንነት፣ ጠቀሜታ እንዲሁም አሠራር የተመለከተ መሆኑን የመ/ቤቱ የትምህርትና ሥልጠና ዳይሬክቶሬት መረጃ ያመለክታል፡፡
ስልጠናውን የተከታተሉት የክልሉ ዋና ኦዲተር መ/ቤት ሰልጣኞች በሰጡት አስተያየት የክዋኔ ኦዲት ለመጀመር የሚያስችልና የነጠላ ኦዲትን ከመደበኛው ኦዲት ጋር አጣጥሞ ለማከናወን የሚረዳ ስልጠና መሆኑንና ይህም ለስራቸው ጠቃሚ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
በስልጠናው 40 የሚሆኑ የክልሉ ዋና ኦዲተር መ/ቤት የኦዲት የስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል፡፡