News

የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የ2007 በጀት ዓመት የኦዲት ሪፖርት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቀረበ

የኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ግንቦት 9 ቀን 2008 ዓ.ም ባደረገው 29ኛ መደበኛ ስብሰባ የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤትን የ2007 በጀት ዓመት የኦዲት ሪፖርት ከፍተኛ የመንግስት ባለሥልጣናትና አመራሮች በተገኙበት አዳምጣል፡፡
የኦዲት ሪፖርቱን ያቀረቡት የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ክቡር ዋና ኦዲተር አቶ ገመቹ ዱቢሶ ሲሆኑ 2፡10 በወሰደው ሪፖረታቸው በርካታ በፋይኔሺያልና ህጋዊነት እንዲሁም በክዋኔ ኦዲት የተገኙ ግኝቶችን አቅርበዋል፡፡
በኦዲት ሪፖርቱ እንደተመለከተው በ2007 በጀት ዓመት ሂሳብ አቅራቢ ከነበሩት 153 የፌዴራል መንግስት ባለበጀት መ/ቤቶች መካከል 145 መ/ቤቶችን ከ24 ቅ/ጽ/ቤቶች ጋር በዋና ኦዲተር መ/ቤት የተቀሩትን 8 መ/ቤቶች ደግሞ በኦዲት ሰርቪስ ኮርፖሬሽን ኦዲት ለማድረግ ታቅዶ የዕቅዱን 100% መሳካቱን ነገር ግን የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ኦዲት ዘግይቶ በመጠናቀቁ የኦዲት ግኝቱ በሪፖርቱ አለመካተቱን ዋና ኦዲተሩ አስረድተዋል፡፡ በክዋኔ ኦዲት በኩል ሊሠራ ከታሰበው 20 ኦዲት ውስጥ የኦዲት ሪፖርታቸው ወጪ የሆኑት 17 የክዋኔ ኦዲቶችና 4 የክትትል ኦዲት ሪፖርቶች መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡
የኦዲት ሪፖርቱን ተከትሎ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በኩል የተዘጋጁ 6 ጥያቄዎች ለዋና ኦዲተሩ የቀረቡ ሲሆን ዋና ኦዲተር ክቡር አቶ ገመቹ ምላሽ ሲሰጡ ከተሰብሳቢ ሂሳብ ጋር ተያይዞ ያሉትን ችግሮች ለመቅረፍ የተጠራቀሙና ለረጅም አመታት ሲንከባለሉ የመጡ ሒሳቦችን እልባት ለመስጠት ሒሳቡ እንዲጠና ተደርጎ በመንግስት እልባት ቢሰጣቸውና የቅርብ ተሰብሳቢ ሂሳቦች ግን ተቋማት ትኩረት ሰጥተው ከሰሩበት ሊስተካከሉ የሚችሉ እንደሆኑ አስረድተዋል፡፡
ከወጪ ጋር በተያያዘ ተቋማት ችግር ውስጥ የሚገቡት በአብዛኛው የግዢ እቅድ ያማያዘጋጁ በመሆኑና የሚያዘጋጁቱም ቢሆኑ በተዘጋጀው እቅድ የማይጠቀሙ መሆናቸውን ገልፀው በተለይ በዚህ እረገድ ያለውን ችግር ለመቅረፍ የመንግስት ግዢና ንብረት አገልግሎት ኤጀንሲ ተቋምን አቅም ማጠናከር እንደሚጠበቅ፣ ከፍተኛ የትምህረት ተቋማት አከባቢ እየተፈጠረ ያለውን ችግር ለመፍታት ለዩኒቨርስቲዎቹ ግዢዎችን የሚፈፅም አካል ቢኖርና ግንባታዎችም በሌላ አካላት ቢገነቡና ዩኒቨርስቲዎቹ በመማር ማስተማሩ ሥራ ላይ ቢያተኩሩ መልካም እንደሆነ ሃሳብ ሰጥተዋል፡፡
በሌላ በኩል ተቋማት ከበጀት በላይና ባልተፈቀደ በጀት ከፍተኛ ወጪ እንዲያወጡ የሚያደርጋቸው ለበጀት አዋጁ አለመገዛት እንደሆነ ገልፀው አንዳንድ አመራሮችም በሚሠጣቸው ማስተካከያ መሰረት ለመፈፀም መንገራገር እንደሚያሳዩ ተናገረዋል፡፡
የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤትን ሪፖርትን ተከትሎ የምክርቤት አባላት በርካታ አስተያየትና ጥያቄዎችን የቀረቡ ሲሆን ዋና ኦዲተር መ/ቤት ላከናወነው ከፍተኛ ተግባር ምስጋናቸውን ለዋና ኦዲተሩ እና ለተቋሙ ሰራተኞች አቅርበዋል፡፡ ምክር ቤቱም የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍና አገሪቱ የተያያዘችውን የዕድገት ጎዳና ለማስቀጠል ከፍተኛ አቅም የሚፈጥርላቸው እንደሆነ ጨምረው ገልፀዋል፡፡
በሌላ በኩል የምክር ቤት አባላት የሰላ ትችታቸውን በመንግስት ተቋማት አመራሮችና ፈፃሚዎች ላይ የሰነዘሩ ሲሆን እንደምክርቤት አስፈፀሚ አመራሮች ማንገራገር መጀመራቸው ተቀባይነት የሌለው መሆኑንና በዚህም ፓርላማውም ቁጭት ውስጥ መግባቱን፣ ምክር ቤቱ የሚያወጣውን አዋጅና ደንብ አስፈፃሚው አካል የማይተገበር ከሆነ ምን እየተከናወነ ነው ሲሉም ጥያቄ ያቀረቡ ሲሆን በተቀመጠው መመሪያና ደንብ መሰረት ህግን ተፈፃሚ በማያደርጉ መ/ቤቶች ላይ እርምጃ የመውስድ ሥራ ምክር ቤቱ በቀጣይ የሚሄድበት ጉዳይ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡
ጫፍ የወጡና ተደጋጋሚ የኦዲት ግኝት ችግር ውስጥ ያሉ ተቋማት ላይ እንደምክርቤት እርምጃ መወሰድ በሚቻልበት አቅጣጫ ላይ ጠንከር ያለ አስተያየቶች በምክር ቤቱ አባላት ተሰንዝረዋል፡፡ እነዚህ ተቋማት ምክር ቤት ቀርበው ሊያስረዱና በጠቅላይ ሚኒስትሩ በኩል እርምጃ ሊወሰድባቸው እንደሚገባም ገልፀዋል፡፡
በሌላ በኩል የምክር ቤት አባላት ለፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ባቀረቡት ጥያቄ የውስጥ ቁጥጥር ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ፤ የሴቶችና ወጣቶችን ሚና በተቋማት ለማጎልበት በኦዲት ምን እየተሰራ እንዳለ፤ የክዋኔ ኦዲትን ይበልጥ አጠናክሮ ለማስቀጠል መ/ቤቱ ምን ያህል ዝግጁነት እንዳላው፤ ክልሎችን ከማገዝና አብሮ ከመስራት አኳያ መ/ቤቱ የሄደበት ርቀት ምን እንደሚመስል፤ ፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት በኦዲት ዘርፍ ያለውን ክፍተት ከመቅረፍ አኳያ ለተቋማት በሚያደርገው ድጋፍ ምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ፤ የአከባቢ ጥበቃን ኦዲት ማድረግ ላይ በቀጣይ ሊሰራ የታሰበ ነገር ካለ እና ተቋሙ ከኪራይ ሰብሳቢነት በፀዳ አግባብ ሥራዎችን ስለመስራታቸው መ/ቤቱ ምን እየሰራ እንደሚገኝ ጥያቄ አቅርበዋል፡፡
ዋና ኦዲተር በቀረቡት ጥያቄዎች ላይ ምላሽ ሲሰጡ በቀጣይ የኦዲት ጥራት ዋና የትኩረት አቅጣጫ ሆኖ እንደሚሰራ እና ለዚህም የኦዲት ጥራት ማረጋገጥ ዳይሬክቶሬት በመ/ቤቱ መቋቋሙንና በቀጣይ በሚወጡ ሪፖርቶች ላይ ይበልጥ አለም አቀፍ የኦዲት ጥራት ደረጃዎችን ጠብቆ ሪፖርት ለማውጣት እየሰሩ እንደሚገኙ ገልፀው ተቋማትም የውስጥ ኦዲት ክፍልን ሊያጠናክሩ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
የሴቶችን ተሳትፎ ከማሳደግ አኳያ መ/ቤቱ የ2008/09 በጀት ዓመት ዕቅድ ሲያዘጋጅ በሁሉም መ/ቤቶች የሴቶች ተሳትፎና እኩል ተጠቃሚነትን ባካተተ መልኩ እንዲታቀድ መደረጉንና ወደስራ መገባቱን ሲያስረዱ በክዋኔ ኦዲት በኩል ለተነሳው የመ/ቤቱ የወደፊት የትኩረት አቅጣጫ የክዋኔ ኦዲትን ይበልጥ አጠናክሮ መቀጠል እንደሆ ገልፀው የክዋኔ ኦዲት ሰፊና ጥልቅ የኦዲት ሥራን የሚጠይቅ በመሆኑ በሚፈለገው ደረጃ ለመሥራት መዘጋጀታቸውን አስረድተዋል፡፡
ፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ክልልሎች ጋር በጋራ መሥራትን በተመለከተ ለተነሳው ጥያቄ ምላሽ ሲሠጡ ክልልሎች ጋር የጋራ የምክክር መድረክ እንዳላቸው ነገር ግን በተያዘው አመት በሚፈለገው ደረጃ አለመስራታቸውን ገልፀው የበጀትና የአቅም ግንባታ ሥራዎችን በተመለከተ በጋራ እየሰሩ እንደሚገኙ አስረድተዋል፡፡
በኦዲት ዘርፍ ያለውን ክፍተት ለማሻሻል የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የኦዲት ተደራጊ መ/ቤቶች የውስጥ ኦዲት ባለሙያዎቻቸውን ሥልጣና የመስጠትና ብቃታቸውን የማረጋገጥ ሥራ እየሰሩ እንደሚገኙ ነገር ግን መ/ቤቱ ከነበረበት የሰው ኃይል እጥረት በሚፈለገው ደረጃ ሳያከናውን እንደቀረ ገልፀው በቀጣይ መ/ቤቱ የሥልጠና ተቋም የማቋቋም ዕቅድ ይዞ እየሠራ ስለሚገኝ በዚህ በኩል የሚፈጠረውን ችግር ለመቅረፍ እንደሚቻል ገልፀው የአከባቢ ኦዲትንም ይበልጥ አጠናክሮ ለመቀጠል እየተሰራ እንደሚገኝና ከኪራይ ሰብሳቢነት ጋር ተያይዞ የተቋሙ ሠራተኞች ለሥነምግባር ችግር እንዳይጋለጡ ዓለም አቀፍ የሙያ ሥነ-ምግባር መመሪያ ተዘጋጅቶ ለሁሉም ኦዲተሮች እንደሚሰጥና በአግባቡ ግንዛቤ እንደሚኖራቸው እንደሚደረግ ገልፀው ከዚህ ባለፈ የሥነምግባር መከታተያ የሥራ ክፍልና በቅርብ ኃላፊዎች ልዩ ክትትል እንደሚያደርጉ አስረድተዋል፡፡
በገቢዎችና ጉሙሩክ ያለውን ችግር ከመቅረፍ አኳያ ዋና ኦዲተሩ የሚሠጡት መፍትሔ ሃሳብ ካለ ተብሎ ለቀረበው ጥያቄ ሃሳባቸውን ሲሠጡ በአገሪቱ በሥራ ላይ የሚገኘው የካሽ ሪጂስተር ማሽን ሙሉ በሙሉ በሁሉም ቦታ ላይ ተግባራዊ አለመደረጉን ገልፀው በአገሪቱ ካሉ 88 ሺ በላይ ማሽኖች ውስጥ ወደ 12 ሺ ገደማ የሚሆኑት ብቻ መረጃ እንደሚያመነጩ ገልፀው ይህም አገሪቱ ልታገኝ የሚገባውን ከፍታኛ ታክስ እያጣች እንደሚገኝና አገልግሎት ላይ ከዋሉ ማሽኖች ውስጥም ጥቂት የማይባሉ ግብር ከፋዮች ህጋዊ ያልሆነ ማሽን እንደሚጠቀሙ አስረድተው በፍጥነት አሠራራችንን ወደ ቴክኖሎጂ መለወጥ ካልቻልን የአገሪቱን እድገት እንደሚጎትተው ገልፀዋል፡፡
በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ወጪ አስተዳደደር ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አምባሳደር መስፍን ቸርነት በመጨረሻ ባቀረቡት ሪፖርት የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ከጊዜ ወደጊዜ ከፍተኛ አምርታ እያመጣ እንደሚገኝና ለአገሪቱ እድገት ብሎም መልካም አስተዳደር መስፈን ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝ ገልፀው በተለይም መ/ቤቱ የዕቅዱን 100% ለማከናወን ያደረገውን ጥረት እና ከዕቅድ ውጪ በልዩ ሁኔታ የቀረቡለትን 6 ተጨማሪ የልዩ ኦዲት ሥራዎችን መስራቱ የተቋሙን ጥንካሬ የሚያሳይ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *