በቀጣይ በጀት ዓመት የኦዲት ጥራትን ለማረጋገጥ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሠራ ተገለፀ
የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ከየካቲት 28 ቀን፣ 2008 ዓ.ም እስከ መጋቢት 3 ቀን፣ 2008 ዓ.ም ባደረገው የ2007/08 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማና የ2008/09 በጀት ዓመት ዕቅድ ዝግጅት ለኦዲት ጥራት ትኩረት ሠጥቶ እንደሚሠራ ተገለፀ፡፡
ክቡር ዋና ኦዲተር አቶ ገመቹ ዱቢሶ በዕቅድ ግምገማና ዝግጅት ወቅት እንደተናገሩት የ2007/08 በጀት ዓመት የኦዲት አፈፃፀም በአብዛኛው የተሣካ እንደነበረ ገልፀው የኦዲት ጥራትን ሊያረጋግጡ የሚችሉ በርካታ ሥራዎች መሠራታቸውን ገልፀዋል፡፡
በዕቅድ ዝግጅት ወቅት የቀጣዩ 5 ዓመት (2008 – 2013 ዓ.ም) ስትራቴጂክ ዕቅድ ለሠራተኛው ቀርቦ ውይይት ከተደረገበት በኋላ የማዳበሪያ ሃሳቦች እንዲካተቱበት ተደርጓል፡፡
የመልካም አስተዳደር ዕቅድም ተዘጋጅቶ ለሠራተኛው የቀረበ ሲሆን በዕቅዱ የተካተቱት ቁልፍ ችግሮች በሚፈቱበት አግባብ ላይ ውይይት ከተደረገ በኋላ እያንዳንዱ የሥራ ክፍል በ2008/09 በጀት ዓመት የዕቅድ ዝግጀት ውስጥ አካቶ እንዲሠራ ተደርጓል፡፡
በሌላ በኩል አብዛኛው የመ/ቤቱ ሥራ በመስክ የሚሠራ እንደመሆኑና ሴቶችን ለአደጋ የሚያጋልጥ መሆኑ ታውቆ በቀጣዩ ዕቅድ የሴቶችን እኩል ተሣታፊነትና ተጠቃሚነት በሚያረጋገጥ አግባብ እንዲታቀድ ተደርጓል፡፡
ከዕቅድ ዝግጅቱ ጎን ለጎን ከአፍሮኤዢያ (AFROSAI) በተወሰዱ የኦዲት ጥራት ማሻሻያዎች (2015 Technical Updates) ሥልጠናውን ተካፍለው በመጡ የፋይናሺያልና ህጋዊነት፣ የክዋኔ ኦዲት እንዲሁም የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ (IT) ባሙያዎች ለኦዲት ባለሙያው አቅርበው የተገኙት ልምዶች ተግባራዊ በሚሆኑበት አግባብ ላይ ምክክርና የልምድ ልውውጥ ተደረጓል፡፡
በዕቅድ ዝግጅቱ መጨረሻ ክብረት ም/ዋና ኦዲተር ወ/ሮ ባዩሽ ተስፋዬ መላ ሠራተኛው በዕቅድ አፈፃፀም ግምገማና በዕቅድ ዝግጅት ወቅት ያሳየውን ከፍተኛ ተነሳሽነት አድንቀው በቀጣይ የበጀት ዓመት የታሰበው እንዲሳካ ሁሉም ሠራተኛ የበኩሉን ሚና እንዲጫወት ያሳሰቡ ሲሆን በሠራተኛው የተነሱ የሰው ሃይልና የግብዓት እጥረቶች ለመፍታት ጥረት እንደሚደረግ ገልፀዋል፡፡
በመጨረሻም ዋና ኦዲተሩ በቀጣይ በጀት ዓመት የኦዲት ሽፋን 100% ለማድረስ እንደሚሠራና የኦዲት ጥራትን ለማሻሻል ብሎም የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍ ጉልህ ትኩረት ተሠጥቶ እንደሚሠራ ገልፀው አሁን በሠራተኛው ያለው የሥራ ተነሳሽነት የታሰበውን ግብ እውን ለማድረግ የጎላ ሚና እንደሚጫወት ተናግረዋል፡፡