የፌዴራል ዋና ኦዲተር አመራሮችና ሠራተኞች ሀምሌ 2 ቀን 2013 ዓ.ም በሆለታ ከተማ አቅራቢያ በሚገኘው የሲባ ፓርክ ችግኞችን በመትከል አረንጓዴ አሻራቸውን አስቀምጠዋል፡፡
የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት፣ የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽንና የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሀን ባለስልጣን ከ 300 በላይ የሚሆኑ ሰራተኞችና አመራሮች በመቀናጀት ባካሄዱት የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር 1,700 የሚሆኑ የተለያዩ ዝርያ ያላቸውን ችግኞች በስፍራው ላይ በመትከል አረንጓዴ አሻራቸውን አስቀምጠዋል፡፡
የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ሰራተኞች ቀደም ሲል በነበሩት ዓመታት በድሬ ግድብ፣ ግራር ጃርሶና በመ/ቤቱ ቅጥር ግቢ የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር በማካሄድ አረንገዴ አሻራቸውን ያስቀመጡ መሆናቸው የሚታወቅ ሲሆን ወደፊትም ይህ ለሀገራችን ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው የአረንጓዴ አሻራ የማስቀመጥ እንቅስቃሴ ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡