News
የፌዴራል ዋና ኦዲተር ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ያቀረቡትን የ2015 የኦዲት ሪፖርት አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጡ

ፌ.ዋ.ኦ፡ሰኔ 14 ቀን 2016፡- የፌዴራል ዋና ኦዲተር ክብርት ወ/ሮ መሠረት ዳምጤ የመ/ቤቱን የ2015 በጀት ዓመት የፋይናንስና ሕጋዊነት እንዲሁም የክዋኔ ኦዲት ሪፖርት አስመልክቶ ሰኔ 11 ቀን 2016 ዓ.ም ለኢ.ፌ.ዲ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ባቀረቡት የኦዲት ሪፖርት ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጡ፡፡

ከተለያዩ የመንግስትና የግል ሚዲያ ተቋማት የመጡ በርካታ ጋዜጠኞች በተገኙበት ሰኔ 14 ቀን 2016 ዓ.ም ለሁለት ሰዓታት በመ/ቤቱ በተካሄደው ጋዜጣዊ መግለጫ የኦዲት ሪፖርቱን በሚመለከቱና ማብራሪያ በሚያስፈልጋቸው ይዘቶች ላይ በክብርት ዋና ኦዲተሯ ዝርዝር ገለጻ ቀርቧል፡፡

የቀረበውን ገለጻ ተከትሎ በስፍራው የተገኙ ጋዜጠኞች ተጨማሪ ማብራሪያ ያስፈልጋቸዋል ባሏቸው ጉዳዮች ዙሪያ ጥያቄዎችን  ያነሱ ሲሆን ከፍተኛ  የኦዲት ግኝቶች በታየባቸው ተቋማትና አካላት ላይ እየተወሰዱ ስላሉ የተጠያቂነት እርምጃዎችና ውጤቶቻቸው ተጨማሪ ማብራሪያ እንዲሰጥ ከሚዲያ አካላቱ ተጠይቋል፡፡

ተጠያቂነትን አስመልክቶ መ/ቤቱ ኦዲት ከማድረግና ግኝቶችን ለሚመለከታቸው አካላት በሪፖርት ከማቅረብ በዘለለ ክስ የመመስረትም ሆነ እርምጃ የመውሰድ ህጋዊ ስልጣን የሌለው መሆኑን ምላሽ የሰጡት ክብርት ዋና ኦዲተሯ የተከናወኑ ኦዲቶችን ተከትሎ በሚቀርቡ የኦዲት ግኝት መረጃዎች መሠረት በቂ ነው ባይባልም ህጋዊ ስልጣን ባላቸው አካላትና በኦዲት ተደራጊ ተቋማቱም ጭምር  ወንጀልንም ሆነ አስተዳደራዊ ግድፈቶችን በሚመለከት በአጥፊዎች ላይ እየተወሰዱ ያሉ የተጠያቂነት እርምጃዎች መኖራቸውን ገልጸው ይህም እንደ ጅምር አበረታች መሆኑንና መጠናከር እንደሚኖርበት ጠቅሰዋል፡፡

የቀረበውን ገለጻ ተከትሎ የሚዲያ አካላቱ ሌሎች የኦዲት ግኝት አስተያየት ደረጃዎችን፣ ተመላሽ ተሰብሳቢ ሂሳቦችን፣ ደንብና መመሪያን ያልተከተሉ ግዥዎችንና ክፍያዎችን፣ የተቋማት በጀት አጠቃቀምን እና ሌሎች በኦዲት ሪፖርቱ የቀረቡ ጉዳዮችን በጥያቄ አንስተው በክብርት ወ/ሮ መሠረት ዳምጤ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል፡፡

በዕለቱ በተካሄደው ጋዜዊ መግለጫ በጥቅሉ 13 ከሚሆኑ የግልና የመንግስት የቴሌቪዥን፣ የራዴዮና የፕሬስ ተቋማት የመጡ ጋዜጠኞች ተሳትፈዋል፡፡

 

The Auditor General Conducted a Press Conference on the Audit Report

OFAG: 21 June 2024:- The Federal Auditor General, H.E Meseret Damtie made press briefing on the 2023/2024 annual audit report which was presented to the Ethiopian Parliament on June 18, 2024.

In the press conference held on June 21,2024 in the Ethiopian Office of the Federal Auditor General, H.E Meseret briefed major parts of the report by pointing out the fundamental audit findings with their outcomes & the progress of the entire auditing activities.

Following to the briefing, the media agents in the conference raised certain auditing matters for further clarification & the Auditor General made more explanation on the issues by signifying the legal mandate of the office concerning the practice of accountability & other auditing facts based on the requests from the media.

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *