News

4ኛው የብሪክስ አገራት ዋና ኦዲተሮች ስብሰባ በሩሲያ፣ በኡፋ ከተማ ተካሄደ:-የፌዴራል ዋና ኦዲተር ክብርት ወ/ሮ መሠረት ዳምጤ ኢትዮጵያን በመወከል በጉባኤው ተገኝተዋል

የዘላቂ ልማት ግቦች አፈፃፀም ኦዲት ላይ ትኩረቱን ያደረገው 4ኛው የብሪክስ አገራት ዋና ኦዲተሮች ስብሰባ በሩሲያ ፌዴሬሽን አካውንትስ ቻምበር አዘጋጅነት በኡፋ ከተማ ከሐምሌ 24 አስከ 26 ቀን 2024 ዓ.ም ተካሄደ፡፡

በመድረኩ የተሳተፉትና ንግግር ያደረጉት የፌዴራል ዋና ኦዲተር ክብርት ወ/ሮ መሠረት ዳምጤ አገራችን ኢትዮጵያ ከቅርብ አመታት ወዲህ በፈጣን የእድገት ለውጥ ላይ እንደምትገኝ አንስተው በተለይም ለረዥም ዓመታት ተቋርጠው የነበሩ ግዙፍ ፕሮጀክቶችው ውጤታማ በሆነ መንገድ መጠናቀቃቸው እና ሌሎች አዳዲስ ፕሮጀክቶችም በማስጀመር የዜጐችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተሠራ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

አያይዘውም የግብርና እና ቱሪዝም ዘርፎችንም ለማሳደግ እየተሰሩ ያሉ ሥራዎች ውጤታማ መሆናቸውንም ዋና ኦዲተሯ ጠቁመው ራስን በምግብ ለመቻል በተሰጠው ልዩ ትኩረት የአገር ውስጥ ፍላጐት ከሟሟለት ባለፈ ለጎረቤት ሀገራት ኤክስፖርት የማድረግ አቅም ላይ ተደርሷል ብለዋል።

እያደገ ያለውን የአገር ኢኮኖሚ የሚመጥን የኦዲት ሥራዎች ከመስራት ጎን ለጎን የዘላቂ ልማት ግቦችን ታሳቢ ያደረጉ በርካታ ኦዲቶችንም ማከናወናቸውን የጠቆሙት ክብርት ወ/ሮ መሠረት ዳምጤ የተሰሩ ኦዲቶች ለህዝብ በድረ-ገጽ ተደራሽ ከማድረግ ባለፈ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይፋዊ ህዝባዊ ስብሰባዎችን በማድረግ የተጠያቂነትና የግልፀኝነት አሠራር እንዲሰፍን እየተሠራ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

ክብርት ወ/ሮ መሠረት ዳምጤ ጨምረው ባቀረቡት ተሞክሮ በዋናነት የፌዴራሉ ዋና ኦዲተር መ/ቤት ከክልሎችና የከተማ አስተዳደር ዋና ኦዲተር መ/ቤቶች ጋር ስላለው ግንኙነት፣ የሥልጣን መሠረቶች፣ ቅንጅታዊ አሠራሮች እና የአቅም ግንባታ ሥራዎች ዙሪያ ገለጻ አድርገዋል፡፡

በተለይም የፌዴራሉ መንግስት ለክልሎች የልማት ማስፋፊያ የሚሰጠውን ድጎማ ኦዲት የማድረግ ስልጣን የፌዴራሉ ዋና ኦዲተር መ/ቤት መሆኑን እና በፌዴራሉና በክልሎች መካከል ይፈጠር የነበረውን የኦዲት ድግግሞሽ ለማስቀረት የነጠላ ኦዲት አዋጅ ወጥቶ መተግበር መጀመሩን አብራርተዋል፡፡

የነጠላ ኦዲት አዋጅ ለአንድ አመት በ4 ክልሎች ብቻ በፖይለት ደረጃ ሲተገበር ከቆየ በኋላ በሁሉም ክልሎችና የከተማ አስተዳደር ዋና ኦዲተር መ/ቤቶች ተግባራዊ ማድረግ መቻሉን ዋና ኦዲተሯ ገልፀው የነጠላ ኦዲት አዋጅ መተግበር ከጀመረ ወዲህ ከክልሎች እና ከከተማ አስተዳደር ዋና ኦዲተር መ/ቤቶች ጋር ያለውን ግንኙነት ይበልጥ እንዲጠናከርና የአቅም ግንባታ ድጋፎች በስፋት እንዲያገኙ ዕድል መፍጠሩን ጠቁመዋል።

ክብርት ዋና ኦዲተር ወ/ሮ መሠረት ከጉባኤው ጎን ለጎን ከተለያዩ የብሪክስ አባል አገራት ዋና ኦዲተር መ/ቤቶች ጋር የሁለትዮሽ ውይይትና የመግባቢያ ሰነዶችን የመፈራረም ስነ-ስርዓቶች ያካሄዱ ሲሆን ከሩሲያ አካውንትስ ቻምበር ጋር የሁለቱ ዋና ኦዲተር መ/ቤቶች በጋራ በሚሰሩባቸው ጉዳዮች ተወያይተው በተለይም በአቅም ግንባታ ሥራዎች ላይ ለመደጋገፍ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

በስነስርዓቱ ላይ በሰሞኑ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን በደረሰው የመሬት መንሸራተት ድንገተኛ አደጋ ሳቢያ የበርካታ ወገኖቻችን ህይወት በማለፉ የሩሲያ ዋና ኦዲተር የተሰማቸውን ሀዘን ለክብርት ወ/ሮ መሠረት ዳምጤ ገልፀዋል።

በተጨማሪም ክብርት ዋና ኦዲተሯ ከቻይና እና ከህንድ ዋና ኦዲተር መ/ቤቶች ጋር ያሉ የሥራ ትብብሮችና መደጋገፎች ተጠናክረው መቀጠል በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ የሁለትዮሽ ውይይት ያደረጉ ሲሆን በውይይታቸውም በዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ከስምምነት ላይ ደርሰው በቀጣይ የመግባቢያ ሠነድ በመፈራረም ወደ ተግባር ለመግባት እንዲያስችላቸው የቴክኒክ ኮሚቴዎችን አቋቁመዋል፡፡

በተመሳሳይ ከብራዚል ኮርት ኦፍ ኦዲት መ/ቤት ጋርም በጋራ ለመሥራት የጐንዮሽ ውይይት ያከናወኑ ሲሆን በዋናነት በቴክኖሎጂ ኦዲት እና በክላይሜት ስካነር ፕሮጀክት /Climate scanner project/ አተገባበር ላይ ለመደጋገፍ ውይይት አድርገው በቀጠይ የመግባቢያ ሰነዶችን ለመፈራረም ከስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡

4ኛው የብሪክስ አገራት ዋና አዲተር መስሪያ ቤቶች ስብሰባ የኡፋ ውሳኔን (Ufa Declaration) በመድረኩ ላይ አጽድቋል፡፡

 

The 4th BRICS Nations’ Auditor Generals Summit in Ufa, Russian Federation: –H.E Meseret Damtie, the Auditor General of SAI Ethiopia Represents the Country.

OFAG: 2 August 2024:- The 4th BRICS countries’ Auditor Generals international meeting was held from July 31 to August 2/2024 in Ufa, the Russian Federation.

In the meeting organized by the Accounts Chamber of the Russian Federation, H.E. Meseret Damtie, the Auditor General, the Office of the Ethiopian Federal Auditor General and other Auditor Generals of BRICS nations with their higher level delegates attended the conference to discuss the group common agenda around significant audit issues.

H.E. Meseret Damtie in her present of the summit made significant speech to aware the gathering about the current development of the country by mentioning basic progresses shown in different economic sectors like agriculture, tourism, and the like.

In her particular focus of the speech, the Auditor General H.E. Meseret Damtie explained in detail that the country is now under way to achieve the world wide sustainable development goals & to fulfill the economic, social and other needs of the people as part of the goals, and also she added her country’s attempts of exporting products from agricultural and other sectors to be on the encouraging track.

Specifying the success of certain economic activities and completed mega projects of the country, H.E. Meseret pointing out the leading role and important contributions of the auditing tasks accomplished by the Office of the Ethiopian Federal Auditor General in the process of assuring public transparency & accountability as well as good governance at both the national and institutional levels.

By indicating multiple activities of the office, the Auditor General H.E Meseret also stated the efficient auditing works & the vast planned capacity building accomplishments of the institution to support the regional audit institutions across the country and different fruitful joint works that the office is practicing with different national stakeholders including the Ethiopian Parliament & other international entities.

In her attend of the gathering, in special parallel talks, H.E. Meseret made effective bilateral discussions and signed memorandums of understanding (MOU) with the Auditor Generals & other higher level officials from different countries such as the Russian Federation, Brazil, China & India, and finally the technical committees were formed for the coming practical reactions, the information notifies.

An additional statement indicates that the 4th BRICS countries’ Auditor Generals meeting approved the Ufa Declaration.

 

   

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *