ሰኔ 16/2010 ዓ.ም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ከሦስት ወራት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ላመጡት ለውጥ የምስጋናና የድጋፍ ሰልፍ በተካሔደበት ወቅት በመስቀል አደባባይ በተፈፀመው የቦንብ ጥቃት በንፁሃን ዜጎች ላይ ለደረሠባቸው የሞትና የአካል ጉዳት የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት አመራሮችና ሠራተኞች የተሠማንን ልባዊ ሃዘን እየገለፅን በአደጋው ጉዳት ለደረሰባቸው ቶሎ ማገገምን፤ ለሟች ቤተሰቦች፣ ወዳጆችና ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ መፅናናትን እንመኛለን፡፡
