21ኛው የዋና ኦዲተሮች እና የባለድረሻ አካላት የምክክር ጉባኤ ከመጀመሩ አስቀድሞ የፌዴራልና የሀረሪ ክልል የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባላትን ጨምሮ የመ/ቤቱን የስራ ኃላፊዎች፣ ሌሎች የክልሉን የስራ ኃላፊዎችና ጉባኤተኞች ያሳተፈ የችግኝ መትከል መረሃግብር በሐረማያ ዩኒቨርስቲ ተካሂዷል።
ከችግኝ መትከል በተጨማሪ የጉባኤው ተሳታፊዎች በሐረር ከተማ የሚገኙ የአብዱል ሸሪፍ ሙዚየም፣ የራምቦ ሀውስ፣ የአዳ ቤት (የአዳ ጋር) እና የባህል ሙዚየሞችን ጎብኝተዋል።