News

የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ለብሔራዊ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት የመገልገያ መሳሪያዎች ድጋፍ አደረገ

የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ጥቅምት 16/2014 ዓ.ም ለብሔራዊ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት የመገልገያ መሳሪያዎች ድጋፍ አደረገ፡፡

የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የኦዲት ዘርፍ ምክትል ዋና ኦዲተር ክብርት ወ/ሮ መሰረት ዳምጤ መ/ቤቱ የማይገለገልባቸውን 8 የስልጠና መስጫ ጠረጴዛዎች፣ እያንዳንዳቸው አራት ስው የሚያስቀምጡ ሶስት ጠረጴዛዎች (group table) እና 5 ላፕቶፖችን ለትምህርት ቤቱ ተወካይ አስረክበዋል፡፡

የትምህርት ቤቱ ተወካይ አቶ አያናው አስረስ በርክክብ ስነስርአቱ ወቅት ትምህርት ቤቱ ለተማሪዎች አገልግሎት የሚውሉ መገልገያዎች ከፍተኛ እጥረት እንዳለበት ገልጸው በፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የተደረገው የቁሳቁስ ድጋፍ እጥረቱን ለማቃለል እገዛ ያደርጋል ብለዋል፡፡ አቶ አያናው በመ/ቤቱ ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ከዚህ ቀደም ብሎ ለጠመንጃ ያዥ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመሳሳይ የቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *