ስድስተኛውን ሀገራዊ ምርጫ ተከትሎ የተመሰረተው የ.ኢ.ፌ.ዲ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አካል የሆነው የመንግስት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤትን ህዳር 08/2014 ዓ.ም ጎበኙ፡፡
የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የኦዲት ዘርፍ ምክትል ዋና ኦዲተር ክብርት ወ/ሮ መሰረት ዳምጤና የመ/ቤቱ የስራ ሀላፊዎች ለቋሚ ኮሚቴው አባላት አቀባበል አድርገዋል፡፡
ክብርት ወ/ሮ መሰረት መ/ቤቱ ከተሰጠው ስልጣን፣ ከተልዕኮውና ከስራ እንቅስቃሴው ጋር በተያያዙ ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ለቋሚ ኮሚቴው አባላት ገለጻ አድርገዋል፡፡ የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ክርስቲያን ታደለ የተደረገው ገለጻ ለቋሚ ኮሚቴው ቀጣይ ስራ መነሻ የሚሆን ግንዛቤን ያስጨበጠ እንደነበረ ገልጸዋል፡፡
የቋሚ ኮሚቴው አባላት በመ/ቤቱ የሚገኘትን የስልጠና ማዕከል፣ የመረጃ ማዕከል እና የስፖርት ማዘውተሪያ ጂምናዚየም ጎብኝተዋል፡፡