የፌደራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ሠራተኞች በአዲስ አበባ ሙዚየም በመገኘት በሙዚየሙ የሚገኙ የተለያዩ ታሪካዊ ቅርሶችንና የባህል ቁሳቁሶችን ጎብኝተዋል፡፡
ግንቦት 15 ቀን 2015 ዓ.ም በመ/ቤቱ ሠራተኞች የተካሄደው የሙዚየም ጉብኝት “የሙዚየሞች ዘለቄታዊነት እና ሁለንተናዊ ደህንነት ” በሚል መሪ ቃል በአለም አቀፍ ደረጃ ለ46ኛ ጊዜ በሀገራችን ደግሞ ለ21ኛ ጊዜ በተለያዩ ፕሮግራሞች እየተከበረ የሚገኘውን የሙዚየም ቀን ምክንያት በማድረግ መሆኑ ታውቋል፡፡
ሙዚየሙን የጎበኙ የተቋሙ ሠራተኞች በጉብኝቱ ማጠቃለያ በሰጡት አስተያየት በሙዚየሙ ባዩት ነገር መደሰታቸውን ገልጸው የሀገርን ታሪክና ባህል ከመረዳት አንጻር ጠቃሚ ግንዛቤ ያገኙበት መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
የመ/ቤቱ ሠራተኞች በተለያዩ ጊዜያት የተለያዩ ግንዛቤዎችን የሚያስጨብጡ ጉብኝቶችን በተለያዩ ቦታዎች ላይ ያደርጋሉ፡፡