በኢ.ፌ.ዴ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የመንግስት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ እና ሌሎች የኦዲት ባለድርሻ አካላት ተሳትፎ በተመረጡ የኦዲት ግኝቶች ላይ የሚካሄዱ ይፋዊ ህዝባዊ የውይይት መድረኮችንና የመስክ ምልከታዎችን የሚመራው የኦዲት ባለድርሻ አካላት ፎረም የ2017 በጀት አመት የስራ መጀመሪያ የውይይት መድረኩን ጥቅምት 27 ቀን 2017 ዓ.ም በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አካሂዷል፡፡
በመድረኩ የፎረሙ የ2016 በጀት አመት የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ የተገመገመ ሲሆን በሰኔ ወር 2016 ዓ.ም በክብርት የፌዴራል ዋና ኦዲተር ወ/ሮ መሠረት ዳምጤ ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የቀረበውን የ2015/2016 ኦዲት አመት የተጠቃለለ የኦዲት ሪፖርት ተከትሎ የሪፖርቱ አካል በሆኑና በተመረጡ የኦዲት ግኝቶች ላይ በ2017 በጀት ዓመት የሚካሄዱ ይፋዊ ህዝባዊ መድረኮችንና የመስክ ጉብኝቶችን በሚመለከት በፎረሙ የታቀዱ ተግባራትም ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡
የመንግስት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴና የፎረሙ ሰብሳቢ የተከበሩ የሺመቤት ደምሴ (ዶ.ር) አማካይነት የቀረበው የ2016 በጀት አመት የፎረሙ የአፈጻጸም ሪፖርት እንደሚያሳየው በፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ቀደም ሲል በተደረጉ ኦዲቶች የታዩ ግኝቶችን መሠረት ያደረጉ ውጤታማ ተግባራት መፈጸማቸው ተመልክቷል፡፡
በበጀት አመቱ ቀደም ሲል በተካሄዱ ኦዲቶች ተቀባይነት የሚያሳጣ አስተያየት ከተሰጠባቸው ተቋማት መካከል 8 የፋይናንሽያልና 13 የክዋኔ ኦዲት በተካሄደባቸው በድምሩ በ21 ተቋማት ላይ ይፋዊ ህዝባዊ ስብሰባዎችን እንዲሁም 6 የገጠር እና 3 የከተማ በድምሩ 9 የመስክ ጉብኝቶችን ማካሄድ መቻሉ በሪፖርቱ ተገልጾ በዚህም በአጥፊዎች ላይ ተጠያቂነትን የማረጋገጥ ጥረቶች መደረጋቸው ተጠቅሷል፡፡
በእቅድ አፈጻጸም ወቅት የታዩ በርካታ ጠንካራ ጎኖች በሪፖርቱ የቀረቡ ሲሆን በሂደቱ ያጋጠሙ ተገቢ የአመራር አካላት በይፋዊ ስብሰባዎች ላይ ያለመገኘት፣ የኦዲት ግኝት ማሻሻያ የድርጊት መርሀ ግብሮችን በወቅቱ ያለመላክ፣ በይፋዊ መድረኮች የሚሰጡ አስተያየቶችን በጊዜውና በአግባቡ ያለመተግበርና ሌሎች ክፍተቶች የአፈጻጸም ተግዳሮቶች እንደነበሩ ተጠቅሷል፡፡
በመቀጠልም የ2017 በጀት አመት እቅድ በተከበሩ የሺመቤት ደምሴ (ዶ.ር) በዝርዝር የቀረበ ሲሆን ካለፈው በጀት አመት የተሻለ አፈጻጸም ለማሳየትና በበጀት አመቱ ተቀባይነት የሚያሳጣ አስተያየት ከተሰጠባቸው ተቋማት መካከል 7 የፋይናንሽያልና 17 የክዋኔ ኦዲት በተካሄደባቸው በድምሩ በ24 ተቋማት ላይ ህዝባዊ ይፋዊ ውይይቶችንና 5 የከተማና 10 የገጠር በድምሩ 15 የመስክ ጉብኝቶችን ለማድረግ መታቀዱን አብራርተው ለዚህም የኦዲት ባለድርሻ አካላቱ ለእቅዱ መሳካት የሚጠበቅባቸውን ድርሻ እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡
የቀረበውን የፎረሙን የአፈጻጸም ሪፖርትና የ2017 እቅድ ተከትሎ በተሰብሳቢዎች በርካታ አስተያየቶች የተሰጡ ሲሆን የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ም/ዋና ኦዲተር ክቡር አቶ አበራ ታደሠ በበኩላቸው በኦዲት ግኝቶች መሠረት ለሚካሄዱ የክትትል ስራዎችና የእርምት እርምጃዎች ተግባራዊነት የኦዲት ባለድርሻ አካላት ድርሻ የጎላ በመሆኑ የፎረሙ አካላት ተሳትፎ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል፡፡
ከተሰብሳቢዎች የተነሱ አስተያየቶችን መሠረት አድርገው ተጨማሪ ሀሳብ የሰጡት ክቡር ም/ዋና ኦዲተሩ የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የኦዲት ስራውን በአይነት፣ በሽፋንና በጥራት የበለጠ ለማጠናከር የሚያስችሉ የሪፎርም ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በተለይም በአቅም ግንባታና በኦዲት ጥራት ላይ ውጤታማ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን በንግግራቸው የጠቀሱት ክቡር ም/ዋና ኦዲተሩ በመ/ቤቱ ስራ ላይ የኦዲት ጥራት ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጠው በመሆኑ የኦዲቱ ተግባር አህጉራዊና አለምአቀፋዊ ተቀባይነት ባለቸው የኦዲት አሠራሮችና ስታንዳርዶች እየተመራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
በመጨረሻም በቀጣይ ጊዜያት ይህንኑ የፎረሙን እቅድ መሠረት ያደረጉ የበጀት አመቱን ተከታታይ ይፋዊ ህዝባዊ የውይይት መድረኮችና የመስክ ጉብኝቶች በማካሄድ የተጠያቂነት ተግባሩን ማጠናከር እንደሚያስፈልግ ከመድረኩ የተገለጸ ሲሆን ለዚህም የኦዲት ባለድርሻ አካላት በባለቤትነት ስሜት ተገቢ ተሳትፎ በማድረግ የድርሻቸውን እንዲወጡ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል፡፡
የኦዲት ባለድርሻ አካላት ፎረም የመንግስት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴን ጨምሮ ሌሎች የኦዲት ባለድርሻ አካላትን በማካተት የተዋቀረ ሲሆን የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት በየአመቱ በበጀት አመት መጨረሻ ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የሚያቀርባቸውን የተጠቃለሉ አመታዊ የኦዲት ሪፖርቶች መሠረት በማድረግ የበጀት አመት ተግባራትን አቅዶ በተመረጡ የኦዲት ግኝቶች ላይ የሚካሄዱ የህዝባዊ ይፋዊ የውይይት መድረኮችንና የመስክ ምልከታዎችን በባለቤትነት ይመራል፡፡
The Audit Stakeholders Forum to be engaged in the New Budget year Plan
The Audit Stakeholders Forum, working with the Public Expenditure Administration & Controlling Affairs Standing Committee of the EFDRE House of Peoples’ Representatives made official meeting to discuss the report of 2023/2024 budget year plan execution, and also to approve the 2024/2025 annual working plan.
As it was specified in the gathering, held on November 6/2024 at the Ethiopian Parliament, the Standing Committee and the auditing stakeholders conducted a total number 21 open public hearings & 9 field observations on several audit findings of certain federal institutions which have been under adverse opinions, confirmed by the audits of the Office of the Federal Auditor General, Ethiopia.
In order to ensure actual accountability and transparency in the utilization of the public resources, appropriate and legal corrective measures were taken on different audited entities based on the audit findings discussed in the public hearings and observed facts in the field reviews, the forum reported.
Discussing the specific tangible outcomes of the accomplished plan, and hindrances faced in the implementation process, the forum members finally admitted the plan achievements to be encouraging.
Next to the report discussed in the meeting, the forum also approved the 2024/2025 action plan in order to conduct about 24 public hearings and 15 field observations based on the selected audit findings of federal institutions with adverse opinions.
Following constructive discussions and suggestions of the forum members on the report & the new plan, H.E Mr. Abera Tadesse, Deputy Auditor General, the Office of the Federal Auditor General-OFAG mentioned the leading role of the forum in the process of ensuring institutional accountability and transparency based on the effective and efficient audit practices.
Indicating the fundamental contributions of the Office of the Federal Auditor General to the actions taken by the forum, H.E. Mr. Abera added that the office is now progressively underway to keep the overall auditing statuses up by implementing globally accepted international audit standards and dedicated capacity building endeavors through institutional reforms that bring sustainable and quality audits.