ቀደም ሲል ለሌሎች የመ/ቤቱ ወኪል ቅርንጫፍ መ/ቤቶች የተሰጠው የአስተዳደርና የህግ ማዕቀፎችን የተመለከተ ስልጠና ባህርዳር ከተማ በሚገኘው የሰሜን ወኪል ቅርንጫፍ መ/ቤት ለሚገኙ አመራሮችና ሠራተኞች ተሰጥቷል፡፡
ከህዳር 17-19/ 2017 ዓ.ም ለሦስት ቀናት የተሰጠው ስልጠና የፌዴራል መንግስት ሰራተኞች አዋጅ፣ የዋና ኦዲተር መ/ቤት የሰራተኞች አስተዳደር ደንብ እንዲሁም የዲሲፕሊን አፈፃፀምና የቅሬታ አቀራረብ ስነ-ስርዓት ደንብን የሚመለከቱ ይዘቶችን የሸፈነ ነው፡፡
የስልጠናው አላማ በሁሉም የዋና ኦዲተር መ/ቤት ወኪል ቅርንጫፍ መ/ቤቶች የሚገኙ አመራሮችና ሠራተኞች የተቋሙን ህጋዊ የአሰራር ስርዓት በአግባቡ ተገንዝበው ወጥ በሆነ አግባብ የኦዲት ስራውን ውጤማነት እንዲያረጋግጡ ለማገዝ መሆኑ የታወቀ ሲሆን 20 የሚሆኑ የወኪል ቅርንጫፍ መ/ቤቱ አመራሮችና ስልጠናውን ወስደዋል፡፡
የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት በተለያዩ የስራ ዘርፎች የሚገኙ የሰራተኞቹን ሙያዊ አቅም ለመገንባት እያደረገ ያለውን ጥረት አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡