የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት በ2015/2016 ኦዲት አመት በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ባለስልጣን የመንግስት ኤሌክትሮኒክ ግዥ ሥርዓትና አሠራሮች ውጤታማነት ላይ ባካሄደው የክዋኔ ኦዲት የታዩ ግኝቶችን በማሻሻል ይበልጥ ውጤታማ ስራ እንዲከናወን ተጠየቀ፡፡
ሚያዚያ 8 ቀን 2017 ዓ.ም የመንግስት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ እና የኦዲት ባለድርሻ አካላት በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ባካሄዱት ይፋዊ ህዝባዊ ውይይት እንደተጠቀሰው ባለስልጣን መ/ቤቱ የመንግስት የኤሌክትሮኒክ ግዥ (e-GP) የአሰራር ሂደት ሰነድ በተሟላ መልኩ ለተገልጋይ ተቋማት ተደራሽ አለማድረጉ፣ በክልል ደረጃ በሚገኙ መ/ቤቶች የኤሌክትሮኒክ ግዥ ስርዓት በተሟላ ሁኔታ ተደራሽ አለማድረጉ፣ የኤሌክትሮኒክ ግዥ ስርዓት ከፋይናንሻል ተቋማትና አሠራሮች ጋር በተሟላ ሁኔታ ያልተሳሰረ መሆኑ፣ ደጋፊ ሰነዶች መሟላታቸው ሳይረጋገጥና የጥያቄው ተገቢነት በአግባቡ ሳይጠና የልዩ ግዥ ፈቃድ በብዛት እየተሰጠ መሆኑ፣ e-GP ከመተግበሩ በፊት የአዋጭነት ጥናት አለመካሄዱ እና በተገልጋዮች ቅሬታና አቤቱታ ስርዓት ላይ የሚታዩትን ጨምሮ ሌሎች የአሠራር ክፍተቶች መኖራቸው በኦዲቱ ተረጋግጧል፡፡
የኦዲት ግኝቶችን ለማሻሻል በባለስልጣን መ/ቤቱ የተወሰዱ እርምጃዎች እንዲብራሩ ከቋሚ ኮሚቴው ተጠይቆ በመድረኩ የተገኙ የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ባለስልጣን አመራሮች ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
ምላሾቹን ተከትሎ ከቋሚ ኮሚቴ አባላቱና ባለድርሻ አካላቱ ጠቃሚ አስተያየቶች የተሰጡ ሲሆን የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ም/ዋና ኦዲተር ክቡር አቶ አበራ ታደሠ በባለስልጣን መ/ቤቱ የተዘጋጀውን የኦዲት ማሻሻያ የድርጊት መርሀ ግብር የተግባራዊነት ደረጃ እና ሌሎች ተጨማሪ ማብራሪያ የሚያስፈልጋቸውን ጉዳዮች በማንሳት በመንግስት ኤሌክትሮኒክ ግዥ ስርዓት የሚካሄደው የጨረታ ሂደት ረጅም ጊዜ የሚወስድ በመሆኑ የኔት ወርክ ችግሮችን ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በመፍታት የሚጓተተውን ሂደት ማሳጠር ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
የፌዴራል ዋና ኦዲተር ክብርት ወ/ሮ መሠረት ዳምጤ የኦዲቱን አለማና የትኩረት አቅጣጫዎች በማስቀደም በሰጡት አስተያየት በባለስልጣን መ/ቤቱ ተወሰዱ የተባሉ የግኝት ማሻሻያ እርምጃዎች በቀጣይ የክትትል ኦዲት የሚረጋገጡ መሆኑን ጠቅሰው በተለይም ከፋይናንስ ተቋማት ጋር ያለውን ቅንጅታዊ አሠራርና ትስስር ማጠናከርና የልዩ ግዥ ፈቃድ አሰጣጥ ሂደቱንም ወጥ ማድረግና የጥያቄውን ተገቢነት በማስረጃ በአግባቡ ማጣራት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
በግዥ ስርአቱ በሚካሄዱ ጨረታዎች ከአቅራቢዎች የሚቀርቡ የመወዳደሪያ ዋጋዎች በተጨባጭ ገበያ ላይ ካሉ ዋጋዎች በእጅጉ የተጋነኑ መሆኑን ምሳሌ በመጥቀስ ያነሱት ክብርት ዋና ኦዲተሯ ይህ ሁኔታ ለብልሹ አሠራርና ሙስና የሚያጋልጥና ለሀብት ብክነት የሚዳርግ በመሆኑ ባለስልጣን መ/ቤቱ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር ቅንጅታዊ አሠራር በመፍጠር በገበያ ጥናት ላይ የተመሠረት ጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር ማድረግ እንደሚገባው አሳስበዋል፡፡
የመንግስት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ የሺመቤት ደምሴ (ዶ.ር) በበኩላቸው መንግስት የኤሌክትሮኒክ ግዥ ሥርዓቱ እንዲዘረጋ የፈለገበት አለማ ሀብት እንዳይባክንና በግዥ ሥርዓቱ ላይ የሚከሰቱ ብልሹ አሠራሮችን ለመከላከል እንዲሁም ግዥውን ዘመናዊና ቀልጣፋ ለማድረግ መሆኑን በማጠቃለያ አስተያየታቸው ጠቅሰው የዚህ አላማ መሳካትም በባለስልጣን መ/ቤቱ ውጤታማ አሠራር ላይ የወደቀ በመሆኑ በኦዲቱ የታዩ ዝርዝር ክፍተቶች በተሟላ ሁኔታ እንዲስተካከሉና ለዚህም በየሶስት ወራት የአፈጻጸም ሪፖርት ለቋሚ ኮሚቴው እንዲቀርብ አቅጣጫ ሰጥተዋል፡፡
PAC requests the e-GP System to be More Effective & Operative
The 2023/2024 audit year performance audit of the Office of the Federal Auditor General, OFAG Ethiopia discloses basic working breakdowns in the electronic government procurement (e-GP) system of the Federal Public Procurement and Property Authority.
Based on the statements discussed during the public hearing, held on April 16, 2025 at the Ethiopian parliament, the authority fails to manage certain fundamental e-GP procedures.
Absence of the e-GP procedural documents in some user institutions, inaccessibility of the system particularly at regional level, lack of integration of the system with appropriate financial and business organizations, time taking procedures of procurement bids, issuance of special procurement privileges without comprehensive investigation of the appropriateness of such exceptional procurement requests, absence of feasibility studies before implementation of the system and other related gaps are among the findings discovered in the audit process, the hearing pointed out.
Following the detail responses and clarification of the executives of the authority, on the measures and attempts taken to improve the findings, H.E. Mrs. Meseret Damtie, the Auditor General and H.E. Mr. Abera Tadesse, Deputy Auditor General, OFAG remarked vital suggestions that can bring such technological system to highly efficient and fruitful public procurement endeavors.
According to the statements of the officials, the authority should make the utilization of the system more advanced by strengthening joint works and proper mechanisms with suitable entities to avoid obstacles that hinder the progress of such valuable platform.
By indicating the advantages of the system, the OFAG officials added that the authority can achieve protecting wastage of public resources and avoiding corrupted interests through strong controlling and follow up practices.