የፌዴራል ዋና ኦዲተር ክብርት ወ/ሮ መሠረት ዳምጤ የኢትዮጵያና የቀጠናውን የዓለም ባንክ ሊድ ገቨርነንስ ስፔሻሊስት ሚስተር ራጁል አዋስቲንን /Rajul Awasthi: Lead Governance Specialist, Ethiopia/ በጽ/ቤታቸው ተቀብለው በማነጋገር የጋራ ውይይት አድርገዋል፡፡
በውይይታቸውም የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት በመንግስት ተቋማት ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ እና መልካም አስተዳደር እንዲሰፍን እየሰራቸው ስላሉ ሥራዎች ክብርት ዋና ኦዲተሯ ያብራሩ ሲሆን በተለይም የመ/ቤቱንም ሁለንተናዊ አቅም ለማሳደግ እየተከናወነ ያሉትን የሪፎርም ተግባራት በተመለከተ ለሚስተር ራጁል አዋስቲን አብራርተውላቸዋል።
የዓለም ባንክ ተጠሪው ሚስተር ራጁል አዋስቲን በበኩላቸው የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት እያከናወናቸው ያሉ ውጤታማ ተግባራትን አድንቀው የተቋሙ እንቅስቃሴ ለሌሎች ሀገራት መሰል ተቋማትም ተሞክሮ የሚሆን በመሆኑ በቀጣይ በሚዘጋጅና ሌሎች ሀገራትን በሚያሳትፍ የበይነ መረብ ውይይት መ/ቤቱ መልካም ተሞክሮዎቹን ለሌሎች ሀገራት እንዲያካፍል ክብርት ዋና ኦዲተሯን ጠይቀዋል፡፡
አያይዘውም የኦዲት ሥራ ይበልጥ እንዲጠናከር እና ከዚህም ጋር ተያይዞ በተቋማት ተጠያቂነት እና መልካም አስተዳደር ይበልጥ እንዲጠናከር ዓለም ባንክ ከፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ጋር ቀጣይም ሥራዎችን እንደሚሠራና የተለያዩ ተገቢ ድጋፎችንም እንደሚያደርግ ሚስተር ራጁል አዋስቲን ገልፀዋል፡፡
The Auditor General Meets the World Bank Lead Governance Specialist of the Region
The Federal Auditor General H.E. Meseret Damtie received the World Bank Lead Governance Specialist of Ethiopia & the surrounding Region, Mr. Rajul Awasthi in her office, and made substantial discussion on basic institutional matters.
In such joint talks, taken place, on August 29, 2024, H.E. Meseret Damtie briefly explained the successful achievements of the Ethiopian Office of the Federal Auditor General by enlightening institutional gains in the auditing areas and the entire reform accomplishments under way in the office as well.
Mr. Rajul Awasthi, in his part of talks, on the other hand, venerated the institutional progresses observed in different working segments of the office & he remarked such evident experiences to be role model for other institutional activities across different countries.
By showing his great feeling of appreciation on institutional attempt of progression, the World Bank Lead Governance Specialist, Mr. Rajul Awasthi promised to facilitate available condition to the office in order to share its model experiences to other global institutions of different countries in the coming scheduled virtual conference, and the necessary supports would also be provided to the office to strengthen institutional performances, Mr. Rajul Awasthi also assured.