Uncategorized

ክብርት ወ/ሮ መሠረት ዳምጤ የፌዴራል ዋና ኦዲተር ሆነው ተሾሙ፤ አቶ አበራ ታደሰም የመ/ቤቱ ም/ዋና ኦዲተር በመሆን ተሾመዋል

 

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ክብርት ወ/ሮ መሠረት ዳምጤ የፌዴራል ዋና ኦዲተር እንዲሁም አቶ አበራ ታደሰ የፌዴራል ም/ዋና ኦዲተር እንዲሆኑ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠ/ሚኒስትር ክቡር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) የቀረበለትን ሹመት አጸደቀ፡፡

ክቡር ጠ/ሚኒስትሩ ግንቦት 26 ቀን 2014 ዓ.ም ወ/ሮ መሠረት ዳምጤን የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ዋና ኦዲተር እንዲሁም አቶ አበራ ታደሰን የመ/ቤቱ ም/ ዋና ኦዲተር ሆነው እንዲሾሙና የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትም ሹመቱን እንዲያጸድቅላቸው መጠየቃቸው ይታወሳል፡፡

በዚህም መሠረት ምክር ቤቱ ዛሬ ሰኔ 2 ቀን 2014 ዓ.ም ባካሄደው 6ኛ ዙር 1ኛ ዓመት በ12ኛ መደበኛ ጉባዔው ክብርት ወ/ሮ መሠረት ዳምጤን የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ዋና ኦዲተር እንዲሁም አቶ አበራ ታደሰን የመ/ቤቱ ምክትል ዋና ኦዲተር በማድረግ የቀረበለትን ሹመት አጽድቋል፡፡

ክብርት ወ/ሮ መሠረት ዳምጤ በፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የኦዲት ዘርፍ ምክትል ዋና ኦዲተር በመሆን ላለፉት 6 ዓመታት በኃላፊነት ሲያገለግሉ የቆዩ ሲሆን ክቡር አቶ አበራ ታደሰ ደግሞ በመ/ቤቱ በተለያየ ደረጃ በክዋኔ ኦዲተርነትና በስራ አስኪያጅነት እንዲሁም በትምህርትና ሥልጠና ዳይሬክቶሬት በዳይሬክተርነት ሲሰሩ የቆዩ ናቸው፡፡

በፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 982/2008 አንቀጽ 6 እና 7 መሠረት የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤትን የሚመሩ ዋና ኦዲተር እና ዋናው ኦዲተርን የሚረዱ ምክትል ዋና ኦዲተሮች በጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅራቢነት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደሚሾሙ መደንገጉ ይታወቃል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *