News

በአፍሪካ እንግሊዝኛ ተናጋሪ ሀገራት ዋና ኦዲተር ተቋማት ቀጠናዊ ማህበር (AFROSAI-E) የተዘጋጀ ወርክሾፕ ተጀመረ

በአፍሪካ እንግሊዝኛ ተናጋሪ ሀገራት ዋና ኦዲተር ተቋማት ቀጠናዊ ማህበር (AFROSAI-E) አዘጋጅነትና  በኢትዮጵያ የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት መድረክ አመቻችነት በማህበሩ አባል ሀገራት ኦዲት ተቋማት እየተተገበሩ በሚገኙት የፋይናንሽያልና ህጋዊነት ኦዲት የጋራ ማኑዋሎች (FAM &CAM) ትግበራ ላይ ያተኮረ ወርክሾፕ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል፡፡

ከማህበሩ የተለያዩ አባል ሀገራት የተውጣጡ 15 ኤክስፐርቶችና የኢትዮጵያ የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የስራ ኃላፊዎች የሚሳተፉበት የምክክር ወርክሾፕ ከነሀሴ 20 ቀን 2016 ዓ.ም አስከ ጳጉሜን 1 ቀን 2016 ዓ.ም የሚቆይ ሲሆን ክቡር አቶ አበራ ታደሠ የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ም/ዋና ኦዲተር በመክፈቻ ስነ-ስርዓቱ ላይ ተገኝተው መድረኩን ከፍተዋል፡፡

ክቡር ም/ዋና ኦዲተር አቶ አበራ ታደሠ በመክፈቻ ንግገራቸው እንደጠቆሙት ወርክሾፑ በተለይም የማህበሩ አባል ሀገራት በጋራ እየተጠቀሙባቸው ያሉትን የፋይናንሽያልና ህጋዊነት ኦዲት ማኑዋሎች (FAM &CAM) የትግበራ ሁኔታ ፈትሾ ጠንካራ ጎኖችን ለማዳበርና በትግበራው ሂደት የገጠሙ ተግዳሮችን ለመቅረፍ የጎላ ሚና አለው ብለዋል፡፡

የአባል ሀገራቱ የኦዲት ተቋማት በወርክ ሾፑ በሚደረጉ ውይይቶች ከሚገኙት ግብአቶች ይበልጥ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ አክለው የገለጹት ም/ዋና ኦዲተሩ የወርክሾፑ ተሳታፊዎች ከተለያዩ ሀገራት የኦዲት ተቋማት የመጡ እንደመሆናቸው ለአጠቃላይ ኦዲት ስራው ጠቃሚ የሆኑ የልምድና ተሞክሮ ልውውጦችን እንደሚያደረጉ እምነታቸውን ገልጸዋል፡፡

በወርክሾፑ መጀመሪያ ላይ በማህበሩ ተወካይ ጆሶፊን ሙኮምባ በ “ኦን ላይን ቨርቹዋል” አማካይነት የማስጀመሪያ ሀሳብ የተሰጠ ሲሆን ከቀጠናዊ ማህበሩ (AFROSAI-E) ተወክለው የመጡ ኤክስፐርቶች በእያንዳንዱ ርዕሰ ጉዳይ ላይ ለውይይት የሚሆኑ ሀሳቦችን በማቅረብ በተሳታፊዎች የሚካሄዱ የእርስ በእርስ ውይይቶችን የሚመሩ መሆኑ ታውቋል፡፡

ወርክሾፑ በቆይታው በዋናነት የፋይናንሽያልና ህጋዊነት ኦዲት ማኑዋሎች (FAM & CAM) ላይ ያተኮረ ውይይት የሚደረግበት ሲሆን “Project management of the Audit, Supervision & review, Change Management and Any other grey areas in the implementation of the methodology” በሚሉና ሌሎች ተዛማጅ የኦዲት ጉዳዮችም ዙሪያ ውይይቶች እንደሚደረጉ ታውቋል፡፡

የአፍሪካ እንግሊዝኛ ተናጋሪ ሀገራት ዋና ኦዲተር ተቋማት ቀጠናዊ ማህበር (AFROSAI-E) በተለያዩ ጊዜያት የአባል ሀገራቱን የኦዲት ተቋማት የኦዲት ስራዎች የሚያጠናክሩ መሰል ወርክሾፖችንና አቅም ማጎልበቻ መድረኮችን በተለያዩ ሀገራት እያዘጋጀ የአባል ሀገራቱን የኦዲት ተቋማት አቅም እያጠናከረ ይገኛል፡፡

 

AFROSAI-E Workshop on Financial and Compliant Audit Manuals (FAM &CAM)

The African Organization of English-Speaking Supreme Audit Institutions (AFROSAI –E) regional workshop is going on in Addis Ababa to discuss the effectiveness of the implementation of the Financial & Compliance Audit Manuals (FAM &CAM).

In the ten days workshop held from August 26 to September 6 /2024, about 15 experts from different African countries under AFROSAI-E including the Audit officials of the Ethiopian Office of the Federal Auditor General are attending the workshop to discuss vital points and share experiences on the contents and the implementation circumstances of the AFROSAI-E common financial & compliance audit manuals (FAM &CAM).

In the opening ceremony of the workshop, H.E Mr. Abera Tadesse, Deputy Auditor General of the Ethiopian Office of the Federal Auditor General made opening speech and he pointed out the objective and significance of the workshop.

Stating the main contents of the workshop, the Deputy Auditor General H.E Mr. Abera Tadesse addressed the participants that the workshop is very supportive particularly to review the contents of the audit manuals and to make detail observation on their practical implementation that strengthen the regional audit practices.

At the beginning of the workshop, through online virtual contact, Josephine Mukomba, expert from AFROSAI-E, notified the actual aim of the regional organization & basic introductory issues of the workshop and she also mentioned main points to be discussed by the participants.

In the workshop organized by the AFROSAI-E & hosted by the Ethiopian Office of the Federal Auditor General-OFAG Ethiopia, experts from the regional organization are assigned to facilitate the workshop, and auditing areas of “Project management of the Audit, Supervision & review, Change Management and Any other grey areas in the implementation of the methodology “will be covered under the main topic of FAM &CAM, the schedule of the workshop informs.

The African Organization of English-speaking Supreme Audit Institutions (AFROSAI –E), as professional regional party, organizes the same workshops and capacity-building platforms to make the auditing practices of the audit institutions under the regional organization very efficient and effective.

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *