በፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የንብረት አስተዳደር፣አያያዝ፣ አጠቃቀምና አወጋገድ ዙሪያ ያተኮረ የሶስት ቀናት ስልጠና ተሰጠ፡፡
የመ/ቤቱ ዋና ኦዲተር ጽ/ቤት ኃላፊን ጨምሮ ከግዥና ንብረት አስተዳደር እንዲሁም ከሰው ሀብት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት የተውጣጡና ስልጠናው የሚመለከታቸው የስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች የተካተቱበት ስልጠና በንብረት አስተዳደር፣ አያያዝ፣ አጠቃቀምና አወጋገድ ሂደት የሚጋጥሙ የስራ ላይ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችል መሆኑ ከመ/ቤቱ የትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
ስልጠናው ከህዳር 24-26/2017 ዓ.ም ለሶስት ተከታታይ ቀናት የተሰጠ ሲሆን በመ/ቤቱ የውስጥ ኦዲት ዳይሬክቶሬት አማካይነት የተሰጠ መሆኑ ታውቋል፡፡
የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት በተለያዩ የስራ ዘርፎች የሚገኙ አመራሮቹንና ሠራተኞቹን ሙያዊ አቅም ለመገንባት በሌሎች ከተቋም ውጪ በሆኑ ስልጠና ሰጪ አካላትና በራሱ የውስጥ አቅም በመጠቀም በርካታ ስልጠናዎችን እያካሄደ ይገኛል፡፡