News

በተቋማዊ አሠራር ላይ የስነ-ምግባር ትግበራ ማካተትን የሚመለከት ሥልጠና ተሰጠ

የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ለመ/ቤቱ የማኔጅመንት አባላት በተቋማዊ አሠራር ላይ መካተት ስለሚገባው የስነ-ምግባር ትግበራ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ፡፡

በስልጠናው መክፈቻ ላይ የተገኙት የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ም/ዋና ኦዲተር ክቡር አቶ አበራ ታደሰ ባስተላለፉት መልዕክት የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት በተቋማት አሠራር ላይ ግልጸኝነትና ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ የሚሠራ እንደመሆኑ በተለይም ከሙስናና ብልሹ አሠራሮች የጸዳ ተቋም በመፍጠር ለሌሎች አርዓያ ሆኖ መገኘት ይኖርበታል ብለዋል፡፡

አያይዘውም የመ/ቤቱ አመራሮችና ሰራተኞችም ተቋማዊ መልካም ስነ-ምግባርን ለማሳደግ በሚከናወኑ ተግባራትና የጥናትና ምርምር ሥራዎች እንዲሁም ብልሹ አሠራሮችን ለማስቀረት በሚደረጉ ጥረቶች ላይ በንቃት እንዲሳተፉ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በመ/ቤቱ የስነ-ምግባር ባለሙያ አቶ ግርማ አይችሉ ስለስነ-ምግባር ተግባራት ማካተት ምንነት፣ ዓለማ፣ ጥቅሞች፣ በማካተቱ ሂደት ከሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች በሚጠበቁ ጉዳዮች ዙሪያ ገለጻ ያደረጉ ሲሆን በስልጠናው የተሳተፉ የማኔጅመንት አባላትም በተነሱ ሀሳቦች ላይ ተጨባጭ ልምዶችን በማንሳት ሰፊ ውይይት አድርገዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *