News

በተቀናጀ የፋይናንስ አስተዳደር መረጃ ሥርዓት (IFMIS) ሂሳብና አፈጻጸም ምርመራ ስርዓት ላይ ያተኮረ ስልጠና ተሰጠ

ከተለያዩ የፋይናንሽያል ኦዲት ዳይሬክቶሬቶች ለተውጣጡ የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ኦዲተሮች በተቀናጀ የፋይናንስ አስተዳደር መረጃ ሥርዓት (IFMIS- Integrated Financial Management Information System) ሂሳብና አፈጻጸም ምርመራ ስርዓት ላይ ስልጠና ተሰጠ፡፡
ስልጠናው በኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የገንዘብ ሚኒስቴር የ IFMIS ፕሮጀክት አማካይነት የተሰጠ ሲሆን ከጥቅምት 23 እስከ ህዳር 2/2015 ዓ.ም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ኢንስቲቲዩት ቅጥር ግቢ በተካሄደው ስልጠና 34 የሚሆኑ የኦዲት ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል፡፡
የሥልጠናው ዋና ዓላማ ሰልጣኝ ኦዲተሮቹ በ IFMIS ስርዓት የሚከናወኑ የፋይናንስ፣ የንብረት እና ሌሎችም ስራዎችን በበለጠ ተገንዝበው የኦዲት ስራውን በተሻለ አቅም እንዲያከናውኑ ማስቻል መሆኑ ታውቋል፡፡
ስልጠናው መሰረታዊ በጀት፣ ጥሬ ገንዘብ፣ የክፍያ ሂሳብ፣ የገቢ ሂሳብ፣ የደመወዝ ዝግጅት፣ የግዥ አፈጻጸም፣ የአላቂ እና ቋሚ ንብረት እና የሂሳብ ማጠቃለያ በሚሉ ይዘቶች ላይ ያተኮረ መሆኑን ከመ/ቤቱ የትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *