News

ማህበሩ የመ/ቤቱን የኦዲት ሥራዎች ደረጃ ለመገምገም የሚያስችል የመግቢያ ስብሰባ አካሄደ

የአፍሪካ እንግሊዝኛ ተናጋሪ ሀገራት ዋና ኦዲተር ተቋማት ማህበር (AFROSAI-E) የኦዲት ጥራት ማረጋገጥ ቡድን የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የኦዲት ሥራ በዓለም ዓቀፍ የኦዲት ደረጃዎች መሠረት ስታንዳርዱን ጠብቆ እየተከናወነ መሆኑን ለመገምገም የሚያስችል የመግቢያ ስብሰባ ከመ/ቤቱ የበላይ አመራሮች ጋር  አካሂዷል፡፡

ነሀሴ 21 ቀን 2016 ዓ.ም በመ/ቤቱ በተካሄደው የግምገማው ማስጀመሪያ የመግቢያ ስብሰባ የፌዴራል ዋና ኦዲተር ክብርት ወ/ሮ መሠረት ዳምጤ የተገኙ ሲሆን የኦዲት ጥራት ቡድኑ የሚያካሂደው የኦዲት ጥራት ግምገማ መ/ቤቱ የሚያከናውነውን የኦዲት ሥራ ይበልጥ ለማሳደግ የጎላ አስተዋጽኦ ያለው በመሆኑ ተገቢ መረጃዎች  ለገምጋሚ ቡድኑ በወቅቱ ይቀርባሉ ብለዋል፡፡

የማህበሩ የኦዲት ጥራት ማረጋገጥ ቡድን በቀጣይ ቀናት በመ/ቤቱ የተለያዩ የስራ ክፍሎች በሚያከናውነው የግምገማ ስራ በተለይም ተቋማዊ ነጻነትና የህግ ማዕቀፎች፣ አደረጃጀትና አስተዳደር፣ የሰው ኃይል፣ የኦዲት ስታንዳርዶችና ዘዴዎች እንዲሁም የኮሙዩኒኬሽን እና የባለድርሻ አካላት ግንኙነት የተመለከቱ ጉዳዮችን መሠረት አድርጎ በተለያዩ የመረጃ ማሰባሰቢያ ዘዴዎች ከስራ ክፍሎች በሚቀርቡለት የሰነድና የቃል መረጃዎች መሠረት ገለልተኛ ግምገማ በማካሄድ ተገቢ የሆኑ አስተያየቶችን የያዘ የግምገማውን አጠቃላይ ሪፖርት ለመ/ቤቱ የበላይ ሃላፊዎች እንደሚያቀርብ ይጠበቃል፡፡

በማህበሩ የሚካሄዱ አለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ መሰል የግምገማ ስራዎች የኦዲት አሠራር ጥራት ለማረጋገጥ በአባል ሀገራቱ የኦዲት ተቋማት ላይ በየጊዜው የሚካሄዱ ሲሆን ከግምገማዎች በኋላ በገምጋሚ ቡድኖች በሚሰጡ ተገቢ የማሻሻያ አስተያየቶችና የግምገማ ደረጃዎች መሠረት ተቋማቱ ጠንካራና አለም አቀፍ የጥራት ደረጃቸውን የጠበቁ ወጥ የኦዲት አሠራሮች እንዲኖራቸው የሚያግዙ ናቸው፡፡

 

AFROSAI-E to Review the Office’s Audit Quality

The African Organization of English-Speaking Supreme Audit Institutions (AFROSAI-E) Audit Quality reviewing team made entry discussion with the officials of the Ethiopian Office of the Federal Auditor General (OFAG) to review the auditing quality of the office.

In the entry discussion made by the AFROSAI-E reviewing team & the appropriate officials of the office, the schedule and specific review requisites of the evaluation were discussed and the Auditor General H.E Meseret Damtie notified all the necessary information sources will be available to make the review process very convenient to the team.

By emphasizing the usefulness and benefits of the review, the Auditor General H.E Messeret adds in her talks that the report based review outcome meaningfully makes the auditing practices of the office more quality that fits international auditing standards.

Particularizing the scheduled frame work of the review, the audit quality reviewing team also specified that the reviewing process will be focusing on the fundamental working areas of the office to observe the existing status of `independence and legal framework, organization and management, human resources, audit standards and methodology, communication and stakeholder management’, target stake holders and other related issues.

In addition to several capacity building endeavors, the African Organization of English -Speaking Supreme Audit Institutions (AFROSAI-E) regularly conducts similar audit quality evaluations in supreme audit institutions of different nations under AFROSAI-E to make their auditing practices more quality and standard.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *