News

መ/ቤቱ ለጋምቤላ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ዋና ኦዲተር መ/ቤት ኦዲተሮች ስልጠና ሰጠ

የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ለጋምቤላ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ዋና ኦዲተር መ/ቤት የኦዲት የስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች በተለያዩ ኦዲት ነክ የአሠራር ስርዓቶች ዙሪያ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ሰጠ፡፡
ከሰኔ 19 እስከ ሰኔ 30/ 2015 ዓ.ም በጋምቤላ ከተማ ለሁለት ተከታታይ ሳምንታት በተካሄደው ስልጠና 50 የሚሆኑ የክልሉ ዋና ኦዲተር መ/ቤት የኦዲት የስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች የተሳተፉ ሲሆን ስልጠናው በፋይናንሽያልና በክዋኔ ኦዲት የተለያዩ አሠራሮች ላይ ያተኮረ መሆኑን ከመ/ቤቱ የትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
በፋይናሽያል ኦዲት ማንዋል /FAM/ እና የህጋዊነት ኦዲት ማንዋል /CAM/ እንዲሁም በአዲሱ የክዋኔ ኦዲት ማንዋል አጠቃላይ አሠራርና እይታ ላይ ያተኮረዉ ስልጠና ሰልጣኝ ኦዲተሮቹ ከፍተኛተሳትፎ ያደረጉበትና ውጤታማ እንደነበር ስልጠናውን የሰጡት የመ/ቤቱ የትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጌትነት አለሙና አሰልጣኝ ኢንስትራክተሮች ቴዎድሮስ ሽመልስ፣ እዮብ ጉታና መልካሙ ባሻ ገልጸዋል፡፡
የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የክልል መንግስታት ዋና ኦዲተር መ/ቤቶችን አቅም ለማሳደግ ባስቀመጠው ዕቅድ መሠረት ከቅርብ ጊዜያት በፊት የትግራይ ክልላዊ መንግስት ዋና ኦዲተር መ/ቤትን ጨምሮ ለተለያዩ ክልሎች ዋና ኦዲተር መ/ቤቶች ተመሳሳይ ስልጠናዎች የተሰጡ ሲሆን ስልጠናዎቹ ተጠናክረው የሚቀጥሉ መሆኑ ታውቋል፡፡

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *