የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ለአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ዋና ኦዲተር መ/ቤት መገልገያ የሚሆኑ የ15 ላፕቶፕ ኮምፒውተሮች ድጋፍ አደረገ፡፡
መጋቢት 16 ቀን 2014 ዓ.ም በመ/ቤቱ በተከናወነው የርክክብ ስነስርዓት ላይ ኮምፒውተሮቹን ያስረከቡት የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የፋይናንስ ፣ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ብርሃኑ አሳዬ ሲሆኑ ወ/ሮ አሚና አደን የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ዋና ኦዲተር መ/ቤት የንብረት ክፍል ኃላፊ ድጋፉን ተረክበዋል፡፡
መ/ቤቱ ቀደም ባሉት ጊዜያት ለተለያዩ የክልል ዋና ኦዲተር ቢሮዎችና ሌሎች መንግስታዊ ተቋማት ተመሳሳይ የላፕቶፕ ኮምፒውተሮች እና የቢሮ መገልገያዎችን ድጋፍ አድርጓል፡፡