News

መ/ቤቱ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ኦዲተር መ/ቤት ኦዲተሮች ስልጠና ሰጠ

የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ለአዲስ አበባ ከተማ ዋና ኦዲተር   መ/ቤት ለሥራ ኃላፊዎችና ለኦዲት ባለሙያዎች በተለያዩ ኦዲት ነክ እና የአሠራር ስርዓቶች ዙሪያ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ሰጠ፡፡

ከነሐሴ 21 እስከ ነሐሴ 27/2016 ዓ.ም በኢትዮጵያ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት በተካሄደው ስልጠና በተለያየ ደረጃ ያሉ የከተማ የአስተዳደሩ ዋና ኦዲተር መ/ቤት የኦዲት ባለሙያዎችና የሥራ ኃላፊዎች ተሳተፈዋል፡፡

ስልጠናው በፋይኔሺያል፣ በክዋኔ እና በገቢ ኦዲት ዓይነቶች (Financial Audit፣ Performance Audit፣ Revenue Audit) ላይ ያተኮረ ሲሆን ከኦዲት ተግባር መነሻ አስከ ኦዲት ሪፖርት አዘገጃጀት ድረስ ያሉ ሂደቶችን ያካተተ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ለአምስት ቀናት በተሰጠው ስልጠና በአጠቃላይ 180 የሚሆኑ ሰልጣኞች የተሳተፉበት እንደነበር ታውቋል፡፡

የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ለተለያዩ ክልሎችና የከተማ አስተዳደር ዋና ኦዲተር መ/ቤቶች በኦዲትና ኦዲት ነክ ጉዳዮች ዙሪያ ተከታታይ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠናዎችን እየሰጠ ይገኛል፡፡

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *