News

መ/ቤቱ ለአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ዋና ኦዲተር መ/ቤት የማኔጅመንት አባላትና ባለሞያዎች ስልጠና ሰጠ

የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ለአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ዋና ኦዲተር መ/ቤት የማኔጅመንት አባላትና ባለሞያዎች በፋይናንሽያል ኦዲት አስተዳደር (FAM) አጠቃላይ አሠራርና እይታ ላይ ያተኮረና የአሰልጣኝ ስልጠናን ያካተተ ስልጠና ሰጠ፡፡

ከታህሳስ 12- 17/04 2015 ዓ.ም በእንጂባራ ከተማ የተካሄደውን በፈተና የታገዘ ስልጠና የሰጡት የመ/ቤቱ የትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት አሰልጣኝ ባለሙያዎች አቶ ቴዎድሮስ ሽመልስና አቶ እዮብ ጉታ ናቸው፡፡

በስልጠናው 10 ሌሎች የመ/ቤቱን ኦዲተሮች የሚያሰለጥኑ እንዲሁም 36 በቀጥታ በስልጠናው የተሳተፉ የአማራ ብሔራዊ ክልልላዊ መንግስት ዋና ኦዲተር መ/ቤት የማኔጅመንት አባላትና ሠራተኞች ተካፍለዋል፡፡

የአሰልጣኝ ስልጠናውን የወሰዱት ሰልጣኞች ወደ መ/ቤታቸው ተመልሰው ለሌሎች ኦዲተሮች በጉዳዩ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እንደሚሰጡ ታውቋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *