የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ለሶማሌ ክልላዊ መንግስት ዋና ኦዲተር መ/ቤት ኦዲተሮች የፋይናሺልና ክዋኔ ኦዲት ሂደትና አተገባበርን በሚመለከት የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ፡፡
ከህዳር 21 -25 ቀን 2017 ዓ.ም ለ 5 ተከታታይ ቀናት በሶማሌ ክልላዊ መንግስት ጅግጅጋ ከተማ በተሰጠው ስልጠና 68 የሚሆኑ የክልሉ ዋና ኦዲተር መ/ቤት የኦዲት የስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ተሳትፈውበታል፡፡
ስልጠናው በተለያዩ የኦዲት አርዕስቶች ላይ የኦዲት ሂደቶችንና የትግበራ ደረጃዎችን ትኩረት አድርጎ የተሰጠ መሆኑን ከመ/ቤቱ ትምህርትና ስልጣን ዳይሬክቶሬት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የክልል ዋና ኦዲተር መ/ቤቶችን አቅም የማጎልበት ስራውን አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡