የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ለሲዳማ ክልላዊ መንግስት ዋና ኦዲተር መ/ቤት ኦዲተሮች በኦዲት ጥራት ማረጋገጥ ዙሪያ የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ፡፡
ከሰኔ 24 -28 ቀን 2016 ዓ.ም ለ 5 ተከታታይ ቀናት በሐዋሳ ከተማ በተሰጠው ስልጠና 12 የሚሆኑ የክልሉ ዋና ኦዲተር መ/ቤት የኦዲት የስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች የተሳተፉ ሲሆን ስልጠናውን የሰጡት አቶ አህመድ ሰዋሊህ የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የኦዲት ጥራት ማረጋገጥ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር እና አቶ ቴዎድሮስ ሽመልስ የመ/ቤቱ የትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት ተጠባባቂ ዳይሬክተር መሆናቸው ታውቋል፡፡
በስልጠናው የኦዲት ጥራት ቁጥጥር፣ ማረጋገጥ፣ እቅድ፣ ክንውን፣ ሪፖርትና የክትትል ሥራ የሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች የተሸፈኑ መሆኑን ከመ/ቤቱ የትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የክልል ዋና ኦዲተር መ/ቤቶችን አቅም የማጎልበት ስራውን አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡
OFAG Training on Audit Quality Assurance
OFAG: 5 July 2024:- The Ethiopian Office of the Federal Auditor General, OFAG provided the capacity building training to the auditors work in the Office of the Sidama Regional State Auditor General, Hawassa, Ethiopia.
According to the information from the Education & Training Directorate of OFAG, the training given for five days, under the main topic of Audit Quality Assurance mainly focused on the Audit Quality Control, Assurance, Plan, Activity, Report, & Follow up.
Additionally, the directorate indicated that the training was given for about 12 audit officials & experts & Mr. Ahimed Sewalih, Director of OFAG Audit Quality Assurance & Mr. Tewodros Shimeles, Acting Director of Education & Training Directorate trained the auditors.
OFAG strongly continues its endeavors with full effort to build the auditing capacity of the regional auditors in various audit areas.