የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት በ2013/14 በጀት ዓመት ውሎና አዳራቸውን በጎዳና ላይ ያደረጉ ህጻናትንና እናቶችን መልሶ ለማቋቋም የተዘረጋውን አሠራር በተመለከተ በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ላይ ያካሄደውን የክዋኔ ኦዲት መሠረት ያደረገ ይፋዊ ህዝባዊ ስብሰባ ተካሄደ፡፡
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የመንግስት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ
ታህሳስ 12 ቀን 2015 ዓ.ም በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ባከሄደው ይፋዊ ህዝባዊ ስብሰባ ላይ እንደተገለጸው ለጎዳና ህይወት የተጋለጡ ህጻናትንና እናቶችን ለመታደግና መልሶ ለማቋቋም የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ማከናወን የሚገባው በርካታ ተግባራት በሚፈለገው መጠን ያለመከናወናቸውን የኦዲት ሪፖርቱ ያሳያል ተብሏል፡፡
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ.ር ኤርጎጌ ተስፋዬን ጨምሮ በመድረኩ ላይ የተገኙት የሚኒስቴር መ/ቤቱ አመራሮች በቋሚ ኮሚቴው ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ በመስጠት ችግሮቹን ለመቅረፍ የሚያስችሉ ዘርፈ ብዙ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
የፌዴራል ዋና ኦዲተር ክብርት ወ/ሮ መሠረት ዳምጤና ም/ዋና ኦዲተሩ ክቡር አቶ አበራ ታደሰ በበኩላቸው የጉዳዩ ዋነና ባለቤት የሆነው ሚኒስቴር መ/ቤቱ ችግሩን በዘላቂነት ለመቅረፍ ማከናወን የሚገባውን በርካታ ተግባራት ያላከናወነ ስለመሆኑ የተካሄደው ኦዲት የሚያሳይ በመሆኑ ቀጣይ የሆኑ የማሻሻያ እርምጃዎችን በመውሰድ ችግሮቹን ለመቅረፍ የሚያስችል ጠንካራ ስራ መስራት አለበት ብለዋል፡፡
የመንግስት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ክርስትያን ታደለና ም/ሰብሳቢዋ የተከበሩ ወ/ሮ አራሬ ሞሲሳ በበኩላቸው ችግሩ በቀላሉ የማይታይና የዜጎችን ህይወት ለመታደግ የሚከናወን ሀገራዊ ጉዳይ በመሆኑ ሚኒስቴር መ/ቤቱ ጠንካራ የአሠራር ስርዓት በመዘርጋት አፋጣኝ እርምጃ መውሰድ እንዳለበት ጠቁመው ሚኒስቴር መ/ቤቱና በመድረኩ የተገኙ ባለድርሻ አካላት ችግሩን ለመቅረፍ የሚያስችሉ የየበኩላቸውን ተግባራት በአጭር ጊዜ ውስጥ በማከናወን ሪፖርት እንዲያቀርቡ አቅጣጫ ሰጥተዋል፡፡
ማስታወሻ፡- የሚከተለውን ሊንክ በመጫን ሙሉውን የመድረኩን ሂደት ለመከታተል ይችላሉ፡፡
https://www.facebook.com/hoprparliament/videos/535971878473450