Uncategorized

ለድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ዋና ኦዲተር መ/ቤት የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ

የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ለድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ዋና ኦዲተር መ/ቤት ኦዲተሮች በገቢ ኦዲት አሠራር ላይ ያተኮረ የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ፡፡

ከታህሳስ 21-25 ቀን 2017 ዓ.ም ለ 5 ተከታታይ ቀናት በድሬዳዋ ከተማ በተሰጠው ስልጠና ስለገቢ ኦዲት ምንነት፣ ጠቀሜታ እንዲሁም ዘመኑ የሚጠይቀውን የኦዲት አሠራር የተመለከተ እና ከእቅድ እስከ ሪፖርት ዝግጅት ያለውን ሂደት የሸፈነ እንደነበር ከመ/ቤቱ የትምህርትና ሥልጠና ዳይሬክቶሬት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ስልጠናውን የተከታተሉት የከተማ አስተዳደሩ ዋና ኦዲተር መ/ቤት ኦዲተሮች በሰጡት አስተያየት ስልጠናው የተለያዩ ተሞክሮዎችን የቀሰሙበት፣ አቅማቸውን ያጎለበቱበት እና ተጨማሪ እውቀት ያገኙበት መድረክ እንደነበርም ጠቁመዋል፡፡

በስልጠናው 52 የሚሆኑ የከተማ አስተዳደሩ ዋና ኦዲተር መ/ቤት የኦዲት የስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች መሳተፋቸው ታውቋል፡፡

የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የክልልና የፌዴራል ከተሞች አስተዳደር  ዋና ኦዲተር መ/ቤቶችን አቅም የማጎልበት ስራውን አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *