News

ለወኪል መ/ቤቶች የሚሰጠው የአስተዳደርና የህግ ማዕቀፎች ስልጠና ተጠናክሮ ቀጥሏል

የፌዴራል ዋና ኦዲተር በደቡብ ወኪል መ/ቤት ሥር ለሚሠሩ ሠራተኞች የዋና ኦዲተር መ/ቤት የአስተዳደርና የህግ ማዕቀፎች ላይ ያተኮረ ስልጠና ሰጥቷል፡፡

በሀዋሳ ከተማ ለሦስት ቀናት በተሰጠው ስልጠና የፌዴራል መንግስት ሰራተኞች አዋጅ፣ የዋና ኦዲተር መ/ቤት የሰራተኞች አስተዳደር ደንብ እንዲሁም የዲሲፕሊን አፈፃፀምና የቅሬታ አቀራረብ ስነ-ስርዓት ደንብ ላይ ያተኮረ መሆኑ ከትምህርትና ሥልጠና ዳይሬክቶሬት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

የስልጠናው ዓላማም በዋናነት ሰራተኞች ሥራቸውን ሲያከናውኑ መብትና ግዴታቸውን አውቀው በህግ አግባብ እንዲሰሩ አቅም ለመፍጠር መሆኑን ተገልጿል፡፡

ከጥቅምት 13 እስከ 15 ቀን 2017 ዓ.ም በተሰጠው ስልጠና 22 የሚሆኑ የፌዴራል ዋና ኦዲተር የደቡብ  ወኪል መ/ቤት  ሠራተኞች  ተሳታፊ ሆንዋል፡፡

የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የውስጥ አቅምን ተጠቅሞ የሰራተኛውን አቅም ለማጎልበት የተለያዩ ስልጠናዎች እየሰጠ የሚገኝ ሲሆን በቀጣይም በቀሪ ወኪል መ/ቤቶች መሰል ስልጠና እንደሚሰጥ ከትምህርትና ሥልጠና የሥራ ክፍል ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *