News

ለመ/ቤቱ ሴት ሰራተኞች መሰረታዊ የኮምፒዩተር አጠቃቀም ስልጠና ተሰጠ

 በፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ለሚሰሩ በዝቅተኛ የትምህርት ደረጃ ላይ ላሉ ሴት ሰራተኞች መሰረታዊ የኮምፒዩተር አጠቃቀም ስልጠና ከጥቅምት 17-21/2012 ዓ.ም ድረስ በመ/ቤቱ የማሰልጠኛ ማዕከል ተሰጠ፡፡

በመ/ቤቱ የሴቶችና ወጣቶች ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት የተሰጠው ይህ ስልጠና አላማው በመ/ቤቱ ዝቅተኛ የትምህርት ደረጃ ያሉ ሴት ሰራተኞች በኮምፒዩተር አጠቃቀም ረገድ ያለባቸውን የአቅም ክፍተት በመሙላት የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ችሎታቸውን ማሳደግ ነው፡፡

በስልጠናው ሰራተኞቹ በማይክሮ ሶፍት ዎርድ፣ ኤክሴልና ፓወር ፖይንት እንዲሁም በኮምፒዩተር አጠቃቀም ላይ መሰረታዊ እውቀትና ክህሎት እንዲጨብጡ ተደርጓል፡፡ ስልጠናው በአብዛኛው በተግባር ልምምድ ላይ እንዲያተኩር በማድረግ ተሰጥቷል፡፡

ስልጠናውን 21 ሴት ሠራተኞች የተካፈሉ ሲሆን አስቀድሞ ያላቸውን የኮምፒዩተር አጠቃቀም ችሎታ መሰረት በማድረግ ለሁለት ተከፍለው እንዲሰለጥኑ ተደርጓል፡፡

ስልጠናውን የመ/ቤቱ የኢንፎርሜሽን ሲስተምስ ሰርቪስ ዳይሬክቶሬት ባለሙያዎች ሰጥተዋል፡፡ በቀጣይም ሁለተኛ ዙር መሰረታዊ የኮምፒዩተር ስልጠና ለመ/ቤቱ ሴት ሰራተኞች ለመስጠት ታቅዷል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *