የፌዴራል ዋና ኦዲተር በምስራቅ ወኪል መ/ቤት ሥር ለሚሠሩ 16 ሠራተኞች በመ/ቤቱ የአስተዳደርና የህግ ማዕቀፎች ላይ መሰረት ያደረገ ስልጠና ተሰጠ፡፡
ከጥቅምት – እስከ ጥቅምት -/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ በሚገኘው የምስራቅ ወኪል መ/ቤት በመ/ቤቱ የህግ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት አማካይነት በተሰጠው የሁለት ቀናት ስልጠና የፌዴራል መንግስት ሰራተኞች አዋጅ፣ የዋና ኦዲተር መ/ቤት የሰራተኞች አስተዳደር ደንብ እንዲሁም የዲሲፕሊን አፈፃፀምና የቅሬታ አቀራረብ ስነ-ስርዓት ደንብ ላይ ያተኮረ መሆኑ ታውቋል፡፡
የስልጠናው ዓላማም በዋናነት የመ/ቤቱ አባላት ሥራቸውን ሲያከናውኑ መብትና ግዴታቸውን አውቀው በተቀመጡ የህግ አግባቦች መሠረት ስራቸውን እንዲያከናውኑ ለማስቻል ነው ተብሏል፡፡
ቀደም ባሉት ቀናት ተመሳሳይ ስልጠናዎች ለሌሎች የመ/ቤቱ ወኪል መ/ቤቶች መሰጠቱ ይታወቃል፡፡