News

ለጤናው ዘርፍ የሚውለውን የግሎባል ፈንድ አፈጻጸም ኦዲት ለማጠናከር የተካሄደው የAFROSAI-E ኦዲት ኤክስፐርቶች አውደ ጥናት ውጤታማ መሆኑ ተገለጸ*በአውደ ጥናቱ ማጠናቀቂያ ተሳታፊዎች የፈንዱን አፈጻጸም ውጤታማነት መቃኘት የሚያስችል ጉብኝት በአዲስ አበባ በሚገኝ አንድ ጤና ጣቢያ ላይ አድርገዋል፡፡

በአፍሪካ እንግሊዝኛ ተናጋሪ ሀገራት የዋና ኦዲተር ተቋማት ማህበር (AFROSAI-E) አስተባባሪነትና አዘጋጅነት እንዲሁም በፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት አስተናጋጅነት ከነሀሴ 12-16 ቀን 2017 ዓ.ም ለአምስት ተከታታይ ቀናት በአዲስ አበባ ሲካሄድ የነበረው አውደ ጥናት ስኬታማ እንደነበር ተገለጸ፡፡

አውደ ጥናቱ ግሎባል ፈንድ (Global Fund)፣ ቫክሲን አሊያንስ (GAVI) እና አፍሮሳይ-ኢ (AFROSAI-E) በላቸው የሶስትዮሽ የጋራ ስምምነት መሠረት በማህበሩ አባል ሀገራት የጤናው ዘርፍ የተለያዩ ተላላፊ የሆኑ በሽታዎችን ለመከላከልና ለመቋቋም ግሎባል ፈንድ እያደረገ ባለው ድጋፍ  አፈጻጸም ላይ በየሀገራቱ የዋና ኦዲተር ተቋማት (SAIs) አማካይነት እየተከናወነ ያለውን ኦዲት ለማጠናከር በሚያስችሉ ቴክኒካዊ ሁኔታዎች ላይ የመከረ መሆኑ ታውቋል፡፡

ከተለያዩ የማህበሩ አባል ሀገራት ዋና ኦዲተር ተቋማት የተሰባሰቡት የአውደ ጥናቱ ተሳታፊ የኦዲት ኤክስፐርቶች በቆይታቸው በጉዳዩ ላይ ያሏቸውን ልምዶችና ተሞክሮዎች የተለዋወጡ ሲሆን በዘርፉ እየተደረገ ባለው የኦዲት እንቅስቃሴ የሚስተዋሉ ጠንካራ ጎኖችና ክፍተቶች ላይ በሰነዶችና በገለጻዎች የተደገፉ ጥልቅ ውይይቶችን አድርገው የወደፊት አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡

ከአውደ ጥናቱ መርሀ ግብር መጠናቀቅ በኋላ ተሳታፊዎች በፈንዱ በታቀፈና በአዲስ አበባ ጤና ቢሮ የየካ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት የጉራራ ጤና ጣቢያ ላይ በመገኘት የፈንዱን አፈጻጸም መቃኘት የሚያስችል ጉብኝት አድርገው በጤና ተቋሙ የስራ ኃላፊዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ገለጻ ተደርጎላቸዋል፡፡

የአውደ ጥናት ቆይታቸው ውጤታማ የነበረና ወደፊት በዘርፉ ለሚከናወኑ የኦዲት ስራዎች መሰረታዊ እገዛ የሚያደርግ መሆኑን በማጠቃለያ አስተያየታቸው የገለጹት ተሳታፊዎች መድረኩን አዘጋጅቶ ላቀረበው ለአፍሪካ እንግሊዝኛ ተናጋሪ ሀገራት የዋና ኦዲተር ተቋማት ማህበር (AFROSAI-E)፣ የኢትዮጵያ የጤና ሚኒስቴር፣ የጤና ጣቢያው የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም መድረኩ ውጤታማ እንዲሆን ስኬታማ መስተንግዶ ላደረገው የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት (SAI Ethiopia) ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

AFROSAI-E Audit Experts’ Workshop Concludes Successfully

The AFROSAI-E workshop aimed at reinforcing the auditing of global health sector funds concluded August 22/2025 after five days of productive and successful discussions.

The workshop held from August 18–22/2025 brought together audit experts from Supreme Audit Institutions (SAIs) under AFROSAI-E.

In their constructive engagement, participants discussed past audit practices in depth, identified strengths and challenges, and exchanged technical experiences to enhance oversight of global funds allocated for preventing HIV/AIDS Tuberculosis, Malaria, and supporting immunization activities.

As part of the program, participants visited a global fund-supported health center in Addis Ababa to observe the achievements of fund utilization.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *