የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደርን በተመለከተ ተሻሽለው የወጡ አዋጅና መመሪያዎችን ለመ/ቤቱ የስራ ኃላፊዎችና ሌሎች ባለሙያዎች ለማስተዋወቅ በሶስት ዙሮች ሲሰጥ የቆየው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡
የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ባለስልጣን እንደገና ተሻሽለው በወጡ አዋጆችና መመሪዎች ዙሪያ ከሐምሌ 21 እስከ ነሐሴ 09 /2017 ዓ.ም በሶስት ዙሮች በተሰጠው ተከታታይ ስልጠና ከመ/ቤቱ የተለያዩ የኦዲት ዳይሬክቶሬቶች እና ስልጠናው ከሚያስፈልጋቸው የድጋፍ የስራ ክፍሎች የተውጣጡ በጥቅሉ 504 ሠልጣኞች የተሳተፉበት ሲሆን ከባለስልጣን መ/ቤቱ የመጡ አሰልጣኝ ባለሙያዎች ስልጠናውን ሰጥተዋል፡፡
የስልጠናው ተሳታፊዎች በስልጠናው ማጠናቀቂያ ላይ በሰጡት አስተያየት ስልጠናው ለስራቸው ተገቢ ድጋፍ የሚሰጡ ጠቃሚ መረጃዎችንና ግንዛቤዎችን ያገኙበትና ግዥና ንብረት አስተዳደር አሠራር ላይ የነበሩ ብዥታዎችን ግልጽ ያደረገላቸው መሆኑን ገልጸው በተለይ የተገኙት ግንዛቤዎች በኦዲት ስራ ላይ በግዥና ንብረት አሠራር ላይ የሚደረጉ ኦዲቶችን በበለጠ ውጤታማነት ለማከናወን ፋይዳቸው የጎላ ነው ብለዋል፡፡
መ/ቤቱ በተለያዩ የስራ ዘርፎች ላይ ለሠራተኞቹ የሚሰጠውን የአቅም ግንባታ ስልጠና አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡