የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የተለያዩ አዳዲስ የአሠራር ሂደቶችን በማካተት ያዘጋጀውን የተሻሻለ የክዋኔ ኦዲት ማኑዋል ለመ/ቤቱ የክዋኔ ኦዲት የስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ማስተዋወቅ የሚያስችል አውደ ጥናት ሀምሌ 30 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ አካሄደ፡፡
ሥልጠናው በአውሮፓ ህብረት የቴክኒክና የፋይናንስ ድጋፍ በአዲስ መልክ የተዘጋጀውን የክዋኔ ኦዲት ማኑዋል ለማስተዋወቅ ታስቦ የተዘጋጀ መድረክ መሆኑ ተገልጿል፡፡
በአውደ ጥናት መክፈቻ ላይ የተገኙት የፌዴራል ዋና ኦዲተር ክብርት ወ/ሮ መሠረት ዳምጤ የአውሮፓ ህብረት ቀድሞ የነበረውን የክዋኔ ኦዲት ማኑዋልና ሌሎች ተቋማዊ የአሠራር ሰነዶችን አሻሽሎ ለማዘጋጀትና ለማቅረብ ካደረገው ድጋፍ ባሻገር የመ/ቤቱን አቅም ለመገንባት እንዲሁም ኦዲቱ ከአለም አቀፍ ምርጥ ተሞክሮዎች ጋር እንዲሳለጥ እና የኦዲት ስራውን የበለጠ ለማሻሻል እየተካሄደ ያለውን ተቋማዊ ለውጥ ቀጣይነት ለማረጋገጥ በጋራ መረዳዳት መርህ መሠረት ለሀገራዊ የመልካም አስተዳደር፣ ተጠያቂነትና ግልጽነት መጎልበት እያደረገ ስላለው ሁለገብ ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
በአዲስ መልክ የተሻሻለውን ማኑዋል ለማስተዋወቅ የተዘጋጀው አውደ ጥናት መ/ቤቱ የክዋኔ ኦዲትን ለማጠናከር ለተያያዘው ቀጣይ ጉዞ ወሳኝ ምዕራፍ መሆኑን የጠቀሱት ክብርት ዋና ኦዲተሯ ማኑዋሉ ለኦዲቱ መተግበሪያ እንደ መመሪያ ከማገልገል ባሻገር የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥ ውጤታማና ብቁ እንዲሆን መ/ቤቱ ነጻና ውጤታማ ኦዲት ለማካሄድ ላለው ቁርጠኝነት እንደ ማዕዘን ድንጋይ ሆኖ የሚያገለግል መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ማኑዋሉ ከአለም አቀፍ የኦዲት ስታንዳርዶች ጋር የተሳለጠ እና ከእቅድ ጀምሮ አስከ ክትትል ድረስ ያሉ የክዋኔ ኦዲት የአሠራር ምዕራፎችን መተግበር የሚያስችሉ ወቅታዊ የሆኑ የአሠራር ማእቀፎችን እና ዘዴዎችን ያካተተ መሆኑን ክብርት ዋና ኦዲተሯ ገልጸዋል፡፡
አያይዘውም የማኑዋሉ መሻሻል በራሱ ግብ ሳይሆን ኦዲተሮች የመንግስት ተቋማትን ቀጣይነት ያለው መሻሻል ለማረጋገጥ በስራቸው ላይ ተገቢና ጥራት ያለው የኦዲት ሪፖርት እንዲያመነጩ ማድረግ የሚያስችል ሂደት መሆኑን በመጥቀስ መ/ቤቱ ማኑዋሉን ከተለዩ የአቅም ግንባታ እንዲሁም የመስክና የምክር አገልግሎት ስራዎች ጋር አቀናጅቶ በተገቢ ሁኔታ ለመተግበር ቁርጠኝነት መኖሩን አረጋግጠዋል፡፡
በማኑዋሉ ትግበራ ሂደት በኦዲት ግኝቶች ላይ የሚሰጡ አስተያየቶች ተጨባጭ ለውጥ እንዲያመጡ ከክልል የኦዲት ተቋማት፣ ከኦዲት ተደራጊዎች እንዲሁም ከህዝብ ተወካዮች ም/ቤትና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ያለውን ቅንጅታዊ አሠራር ማጠናከር እንደሚገባም ክብርት ወ/ሮ መሠረት ዳምጤ ገልጸዋል፡፡
ዋና ኦዲተሯ በንግግራቸው ማጠቃለያ በሰጡት ሀሳብ አውደ ጥናቱ የማኑዋሉን ይዘቶች አስመለክቶ የሀሳብና የልምድ ልውውጥ የሚደረግበት መድረክ በመሆኑ ተሳታፊዎች ሰፊና ጥልቅ ውይይት እንዲያደርጉና ወደፊት በኦዲት ስራቸው የሚጠቀሙበትን ማኑዋልም ለመንግስት ተቋማት የአሠራር ለውጥና መሻሻል ተገቢ አስተዋጽኦ በሚያደርግበት አግባብ በስራ ላይ እንዲያውሉት አሳስበው በማኑዋሉ ዝግጅት ሂደት ለተሳተፉ የአውሮፓ ህብረት እና የመ/ቤቱ የክዋኔ ኦዲት ቴክኒካል ቡድን አባላት በድጋሜ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
መ/ቤቱ ከቅርብ ጊዜ በፊት በአዲስ መልክ የተሻሻለውን የፋይናንሽያል ኦዲት ማኑዋል ለማስተዋወቅ ተመሳሳይ አውደ ጥናት ማካሄዱና ይህንኑ ተከትሎም ለፋይናንሽያል ኦዲተሮች ተከታታይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎችን መስጠቱ የሚታወቅ ሲሆን ይህንን የተሻሻለ የክዋኔ ኦዲት ማኑዋል ይዘቶች አስመልክቶም የክዋኔ ኦዲተሮች የሚሳተፉባቸው ተመሳሳይ የስልጠና መርሀ ግብሮች እንደሚካሄዱ ይጠበቃል፡፡
OFAG Officially Introduces the Improved Performance Audit Manual
*In the opening session of the dissemination workshop, the Auditor General Meseret Damtie prominently recommended the auditors to implement the Manual under proper utilization of the improved technical tools.
The Office of the Federal Auditor General, Ethiopia, OFAG formally introduced the newly amended performance audit manual in the dissemination workshop held on August 6/2025 in Addis Ababa.
H.E Mrs. Meseret Damtie Chaniyalew, the Auditor General made the improved performance audit manual official at the time of her present in the opening session of the workshop, and she also conveyed her hot gratitude to the European Union for its institutional progress based and multi propose supports including the provision of the manual.
Referring amendment basics of the manual, the auditor General indicated it has been professionally and meaningfully organized through inclusion of contemporary performance audit methodologies, working frame works and significant working tools which are aligned with internationally accepted audit standards.
In line with this fact, H.E Mrs. Meseret added that the office is highly committed to make the manual more practical by strengthening the overall institutional reforms and capacity building endeavors thorough sustainable joint efforts of target stakeholders including regional audit institutions, the parliament, the auditees, suitable public sectors, and other partners.