News

መስሪያ ቤቱ ለአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ዋና ኦዲተር መ/ቤት የአቅም ግንባታ ሥልጠና ሰጠ

የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ለአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ዋና ኦዲተር መ/ቤት ኦዲተሮች የሂሳብና ህጋዊነት እንዲሁም የክዋኔ ኦዲት ማኑዋሎች አተገባበር ላይ የአቅም ግንባታ ሥልጠና ሰጠ፡፡

ከሰኔ 16-20 ቀን 2017 ዓ.ም በሰመራ ከተማ በተሰጠው ሥልጠና በጠቅላላ 51 የሚሆኑ የክልሉ ዋና ኦዲተር መ/ቤት የፋይናንሽያልና የክዋኔ ኦዲት ኦዲተሮች መሳተፋቸው ተገልጿል፡፡

ስልጠናው በተሻሻለው አዲሱ የፋይናንስና ኦዲት ማኑዋል እና የክዋኔ ኦዲት ማንዋል ላይ ግንዛቤ ለማስጨበጥ የተካሄደ መሆኑን ከመ/ቤቱ የትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የክልል ዋና ኦዲተር መ/ቤቶችን አቅም የማጎልበት ሥራውን በተለያዩ አግባቦች አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *