የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት በምዕራብ ወኪል መ/ቤት ስር ለሚሠሩ ሠራተኞች የመ/ቤቱን የአስተዳደርና የህግ ማዕቀፎች በተመለከተ ቀጣይ ስልጠና ሰጠ
በጅማ ከተማ ለሦስት ቀናት በተሰጠው ስልጠና የፌዴራል መንግስት ሰራተኞች አዋጅ፣ የዋና ኦዲተር መ/ቤት የሰራተኞች አስተዳደር ደንብ እንዲሁም የዲሲፕሊን አፈፃፀምና የቅሬታ አቀራረብ ስነ-ስርዓት ደንብን የሚመለከቱ መሠረታዊ ጉዳዮች በስልጠናው ተነስተዋል፡፡
ስልጠናው በዋናነት በሁሉም የዋና ኦዲተር መ/ቤት ቅርንጫፍ ወኪል መ/ቤቶች የሚሠሩ ሰራተኞች የተቋሙን የአሰራር ስርዓት ተገንዝበው መብትና ግዴታቸውን አውቀው በህግ አግባብ እንዲሰሩ አቅም ለመፍጠር መሆኑን ተገልጿል፡፡
ከህዳር 4 እስከ 6 ቀን /2017 ዓ.ም በተሰጠው ስልጠና 18 የሚሆኑ የምዕራብ ወኪል መ/ቤት ሠራተኞች ተሳታፊ መሆናቸውን ከመ/ቤቱ የትምህርትና ሥልጠና ዳይሬክቶሬት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የውስጥ አቅምን ተጠቅሞ የሰራተኛውን አቅም ለማጎልበት የተለያዩ ስልጠናዎች እየሰጠ ይገኛል፡፡