የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ከሀረሪ ክልላዊ መንግስት ዋና ኦዲተር መ/ቤት ለመጡ በተለያዩ የስራ ዘርፎች የሚገኙ የስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች የመ/ቤቱን አሠራሮች በሚመለከት ልምድና ተሞክሮውን አካፍሏል፡፡
ከመስከረም 20 -21/2017 ዓ.ም በፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት በመገኘት የአሠራር ልምድና ተሞክሮ የወሰዱት የክልሉ ዋና ኦዲተር መ/ቤት የስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች በተለይም በእቅድ ዝግጅት፣ በህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን እንዲሁም በለውጥና መልካም አስተዳደር ዙሪያ ያሉትን የመ/ቤቱን አሠራሮች በሚመለከት ጠቃሚ ልምዶችን ወስደዋል፡፡
የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የተለያዩ የኦዲትና የድጋፍ ዘርፍ አሠራሮቹን በተመለከተ የክልሎችን ጨምሮ ለተለያዩ ተቋማት ውጤታማ የሆኑ የልምድና ተሞክሮ የማከፈል ተግባር እያከናወነ የሚገኝ ሲሆን ከሀረሪ ክልላዊ መንግስት ዋና ኦዲተር መ/ቤት የመጡት የስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎችም ባካሄዱት የልምድና ተሞክሮ ልውውጥ ሂደት ጠቃሚ አሠራሮችን መቅሰማቸው ተመልክቷል፡፡