News
የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የመ/ቤቱ የ2015/2016 የኦዲት ተግባር አፈጻጸም ውጤታማ መሆኑን ገለጸ

ፌ.ዋ.ኦ፡ ሰኔ 11 ቀን 2016፡- የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት በ2015/2016 ኦዲት አመት በተለያዩ ተቋማት ላይ ያካሄዳቸው ኦዲቶች አፈጻጸም እቅዱን ያሳካና ውጤታማ እንደነበር ተገለጸ፡፡

ይህ የተገለጸው የፌዴራል ዋና ኦዲተር ክብርት ወ/ሮ መሠረት ዳምጤ ሰኔ 11 ቀን 2016 ዓ.ም በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ቀርበው የመ/ቤቱን የ2015/2016 ኦዲት አመት የተጠቃለለ የሂሳብና ህጋዊነት እንዲሁም የክዋኔ ኦዲቶች አፈጻጸም ሪፖርት ባቀረቡበት መድረክ ነው፡፡

ክብርት ዋና ኦዲተሯ በመድረኩ ባቀረቡት ዝርዝር አመታዊ የኦዲት ሪፖርት መሠረት የመ/ቤቱ ተጠሪ በሆነው የሂሳብ ምርመራ አገልግሎት ኮርፖሬሽን አማካይነት በመንግስት ልማት ድርጅቶች ላይ እንዲከናወኑ የታቀዱ ኦዲቶችን ጨምሮ በፋይናንስና ህጋዊነት ኦዲት የእቅዱን 94.44 በመቶ አፈጻጸም መመዝገቡ ተገልጿል፡፡

ከዚህም ሌላ መ/ቤቱ በኦዲት አመቱ ባከናወናቸው የክዋኔ ኦዲቶች መሠረት የእቅዱን 97.72 በመቶ አፈጻጸም ማመዝገብ መቻሉንና ልዩ ኦዲትን በተመለከተም መ/ቤቱ በኦዲት አመቱ 11 ልዩ ኦዲቶችን ለማድረግ ያቀደ ቢሆንም ከተለያዩ ተቋማትና አካላት 26 የልዩ ኦዲት ጥያቄዎች በመቅረባቸው ከእቅድ በላይ በሆነ መልኩ 23  ኦዲቶች ማከናወን መቻሉን ክብርት ዋና ኦዲተር ወ/ሮ መሠረት ዳምጤ በሪፖርታቸው ገልጸዋል፡፡

በኢትዮጵያ መንግስትና በአለም ባንክ ስምምነት መሠረት በተለያዩ ክልሎች በሚገኙ ወረዳዎች በሚካሄዱ የተለያዩ ማህበረሰብ አቀፍ ፕሮግራሞች ላይ በኦዲት አመቱ 337 የተከታታይና የአፈጻጸም ማረጋገጫ ኦዲት ለማድረግ ታቅዶ የነበረ መሆኑን ጨምረው የገለጹት ክብርት ዋና ኦዲተሯ ከእቅድ በላይ በሆነ ሁኔታ 345 በማከናወን 102.37 በመቶ አፈጻጸም ማስመዝገብ መቻሉን ጠቅሰዋል፡፡ 

በኦዲት አመቱ በተደረጉት የተለያዩ ኦዲቶች መሠረት ከታዩ ግኝቶች መካከል የጥሬ ገንዘብ ጉድለት፣ የውዝፍ ተከፋይ ሂሳቦች በወቅቱ አለመሰብሰብና አለማወራረድ፣ የግብር እና ቀረጥ ገቢን አለመሰብሰብ፣ ህገወጥ ግዥዎችን መፈጸም፣ የውስጥ ገቢን አለመሰብሰብ፣ በጀትን በአግባቡ አለመጠቀም፣ በብልጫ ክፍያዎችን መፈጸም፣ ተገቢ ያልሆነ የንብረት አስተዳደርና አጠቃቀም አሠራር መኖር፣ ተገቢ የአሠራር ስርዓት አለመዝርጋትና አለመተግበር፣ የቅንጅታዊ አሠራሮች አለመኖር፣ ፕሮጀክቶችን በተያዘላቸው በጀትና ጊዜ አለማጠናቀቅ፣ ተግባራትን በእቅድ መሠረት አለመፈጸም ዋና ዋናዎቹ መሆናቸውም ባቀረቡት ሪፖርት ተገልጿል፡፡

ከኦዲቱ በኋላ መሠረታዊ የኦዲት ግኝት በታየባቸውና በተመረጡ ተቋማት ላይ በም/ቤቱ የመንግስት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አማካይነት በተካሄዱ ይፋዊ ህዝባዊ ውይይት መድረኮችና የመስክ ምልከታዎች በቋሚ ኮሚቴ አባላትና ባለድርሻ አካላት ተገቢ የግኝት ማሻሻያ አስተያየቶች መሰጠታቸውንና ከዚያ ባለፈም ጉልህ የሆኑ የህግና የአሠራር ጥሰት በፈጸሙ ተቋማት፣ የስራ ኃላፊዎችና ሌሎች አካላት ላይ የተለያዩ ደረጃቸውን የጠበቁ የተጠያቂነት እርምጃዎች በሚመለከታቸው ህጋዊ አካላት በኩል መወሰዳቸውንም ክብርት ወ/ሮ መሠረት በሪፖርታቸው አመላክተዋል፡፡

በኦዲቱ ሂደት ያጋጠሙ ችግሮችን በሪፖርታቸው በዝርዝር ያነሱት ክብርት ወ/ሮ መሠረት ዳምጤ የተቀናጀ የፋይናስ አስተዳደር የመረጃ ስርዓት (IFMIS)፣ የኤሌክትሮኒክስ የመንግስት ግዥ ስርዓት(EGP) እንዲሁም የገቢዎችና ጉምሩክ የአሠራር ስርዓት መቆራረጥ፣ በጸጥታ ችግር ምክንያት ኦዲቶችን በእቅድ መሠረት ለማከናወን አለመቻል እና  በቢሮዎች እድሳት ምክንያት ማስረጃ ማቅረብ ባለመቻሉ ኦዲት ያልተደረጉ ተቋማት መኖራቸው ያጋጠሙ ችግሮች መሆናቸውን አንስተዋል፡፡

አያይዘውም የተቋም ኃላፊዎች በመውጫ ስብሰባ ወቅት አለመገኘት እና የኦዲት ጊዜን የተለያዩ ምክንያቶችን በማቅረብ ማጓተት፣ ለኦዲት የስራ ወረቀቶችና ረቂቅ ሪፖርቶች በወቅቱ ምላሽ አለመስጠት፣ የሂሳብ ሪፖርቶችን በወቅቱ ዘግቶ አለማቅረብ እንዲሁም ለኦዲት ስራ የሚሆን ቢሮና የሂሳብ ሰነዶችን በተቀመጠው ጊዜ ገደብ ውስጥ ለኦዲተሮች አዘጋጅቶ አለማቅረብ በኦዲቱ ወቅት ከገጠሙ ችግሮች መካከል የሚጠቀሱ መሆናቸውን ጨምረው የገለጹት ክብርት ዋና ኦዲተሯ ችግሮቹን ከሚመለከታቸው የስራ ኃላፊዎች ጋር በወቅቱ በመነጋገር ለመፍታት ጥረት መደረጉን ጠቅሰዋል፡፡

የተከናወነውን የኦዲት ተግባር ለማሳካት የመ/ቤቱ የድጋፍ ዘርፍ ሚና ከፍተኛ መሆኑንና አፈጻጸሙም ተጨማሪ ስኬት የተመዘገበበት መሆኑ በቀረበው ሪፖርት የተጠቀሰ ሲሆን በተለይም የመ/ቤቱን የሪፎርም ስራ ለማጠናከር የተካሄደውና በማጠናቀቂያ ምዕራፍ ላይ የሚገኘው የመ/ቤቱ የህንጻ እድሳትና የስራ አካባቢን ይበልጥ ምቹ የማድረግ (Renovation) ተግባር ስኬታማ መሆኑንና በቅርብ ጊዜ ሙሉ ለሙሉ ተጠናቆ በስራ ላይ እንደሚውል ተገልጿል፡፡

ተቋማዊውን  አልፎም ሀገር አቀፋዊውን ኦዲት ወቅቱን ከጠበቀ አለምአቀፋዊ ስታንዳርድ ጋር ለማጣጣም እየተሰሩ ያሉ ዘርፈ ብዙ ጥረቶችን ለማጠናከርም በኦዲት አመቱ ለክልል ዋና ኦዲተር መ/ቤቶች እየተደረገ ያለውን የስልጠናና ግብአት ድጋፍ ጨምሮ በአዳዲስ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ እና የሰው ኃይል አቅም ግንባታ፣ በሴክተር ዘለል ስራዎች፣ ከባለድርሻ አካላት ጋር በተደረጉ ቅንጅታዊ አሠራሮች፣ በመረጃ ተደራሽነት እና በሌሎች ተቋማዊ አፈጻጸሞች የኦዲት ስራውን ፍሬያማ ያደረጉ ስራዎች መከናወናቸውም ተመልክቷል፡፡

ከሪፖርቱ በኋላ አስተያየታቸውን የሰጡት የም/ቤት አባላት በበኩላቸው የመ/ቤቱ የኦዲት አፈጻጸም በተለይም ተጠያቂነትን ከማረጋገጥ አንጻር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ የመጣ፣ እቅዱን ያሳካና ውጤታማ መሆኑን ጠቅሰው ተጨማሪ ማብራሪያ የሚያስፈልጋቸውን ጉዳዮች በማንሳት በክብርት ዋና ኦዲተር ወ/ሮ መሠረት ዳምጤና በክቡር ም/ዋና ኦዲተር አቶ አበራ ታደሠ ምላሽና ተጨማሪ ገለጻ ተሰጥቶባቸዋል፡፡

በመጨረሻም የመንግስት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ የሺመቤት ደምሴ(ዶ.ር) በበኩላቸው የክዋኔ ኦዲት አፈጻጸም እየተሻሻለ መምጣቱን ጨምሮ፣ በመረጃ አያያዝ፣ በቅንጅታዊ አሠራር፣ በልምድ ልውውጥ፣ የስራ አካባቢን ምቹ በማድረግ ረገድ እና በሌሎች አሠራሮች እየታየ ያለው የመስሪያ ቤቱ ጥረት በጠንካራ ጎን የሚታይ መሆኑን ጠቅሰው በኦዲት ተደራጊ ተቋማትና በሌሎች ባለድርሻ አካላት በኩል መፈጸም ይገባቸዋል ያሏቸውን ነጥቦች አንስተዋል፡፡

 

The House Recognizes the Office’s Productive Audit Accomplishment

OFAG: 18 June 2024:- The House of People’s Representatives of the Federal Democratic Republic of Ethiopia-HOPR officially acknowledged the 2023/2024 audit year effective audit accomplishments of the Ethiopian Office of the Federal Auditor General, OFAG Ethiopia.

In the house general assembly, held on June 18, 2024, the Federal Auditor General, H.E Mrs. Meseret Damtie provided the 2023/2024 audit year annual audit report to the congress & pointed out the details of the audit activities & outcomes by specifying the total number of audits conducted under each audit type & the findings of a number of financial, performance & other types of audits.

As has been identified in the audit report, by covering a total number of 151 governmental institutions under financial and regulatory audits in the audit year, the office has achieved 94.44% of the plan.

On the other hand, the office conducted a total number of 43 performance audits including 11 follow up reviews in the audit year, and then 97.72 % of the plan has been achieved, the report additionally specified.

According to additional accounts of the report, the office has reached better achievements in the special audits carried out on occurrences of different governmental organizations, and it has also attained marvelous outcomes in the audits conducted on the accomplishments of grant programs over the country.

By mentioning major audit findings, the Auditor General H.E Meseret Damtie indicated that a number of serious working gaps & illegal actions were identified in various financial & property administration systems of several governmental institutions.

In addition to the achievements verified in the audit areas, as part of the report, the Auditor General also stated the institutional successful achievements of supporting activities observed in the audit year.

After the final statements of the audit report, the congress discussed the audit facts, and finally recognized the report by mentioning fruitful auditing improvements shown in the attempts of performance audits in particular and encouraging total progress of the office in general.

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *