የፌዴራል ዋና_ኦዲተር መ/ቤት ለፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች፣ ለአቃቢ ህጎች፣ ለሌሎች ለባለድርሻ አካላት እና ለሚመለከታቸው የመ/ቤቱ የስራ ኃላፊዎች በልዩ ኦዲት አሰራር እና ግልፀኝነት እንዲሁም ተጠያቂነትን ላይ ያተኮረ ስልጠና አካሄደ፡፡
ከታህሳስ 1 አስከ 2 ቀን 2016 ዓ.ም ለ2 ቀናት በቆየው ስልጠና በጥቅሉ 46 የሚሆኑ ሰልጣኞች ተሳትፈዋል፡፡
ስልጠናው በዋናነት የልዩ ኦዲት አሰራርን አስመልክቶ ግንዛቤ ለማስያዝና በአሰራር ሂደት ውስጥ የሚያጋጥሙ ችግሮችን በመለየት የጋራ መፍትሄ ሀሳብ ለማስቀመጥ ታስቦ የተዘጋጀ ሲሆን ሰልጣኞች በስልጠናው ወቅት ያደረጉት ተሳትፎም ጠንካራ መሆኑን ከመ/ቤቱ የትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተገኘው መረጃ ይጠቁማል፡፡
መ/ቤቱ ለእራሱ ኦዲተሮች እያደረገ ካለው ተከታታይ የአቅም ግንባታ ስራ በተጨማሪ የባለድርሻ ተቋማት አመራሮችንና ባለሙያዎችን አቅም ለማሳደግ የተለያዩ ሙያዊ ስልጠናዎችን እየሰጠ ይገኛል፡፡