የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ለሀረሪ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ዋና ኦዲተር መ/ቤት የኦዲት የስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች በተለያዩ ኦዲት ነክ እና የአሠራር ስርዓቶች ዙሪያ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ሰጠ፡፡
ጥቅምት 5 ቀን 2016 ዓ.ም ተጀምሮ አስከ ጥቅምት 11 ቀን 2016 ዓ.ም የቆየውና በሀሮማያ ዩኒቨርሲቲ በተሰጠው ስልጠና 63 የሚሆኑ የክልሉ ዋና ኦዲተር መ/ቤት የኦዲት የስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል፡፡
ስልጠናው በፋይናንሽያል ኦዲት ማንዋል ላይ ያተኮረ መሆኑን ከመ/ቤቱ የትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የተለያዩ የክልል መንግስታት ዋና ኦዲተር መ/ቤቶች አመራሮችንና ባለሙያዎችን አቅም አስፈላጊ በሆኑ ስልጠናዎች እየገነባ መሆኑ ይታወቃል፡፡