የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ባለሙያዎች የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤትን በመጎብኘት በኢንፎርሜሽን ሲስተም ሰርቪስ የአሠራር ሥርዓትና መሠረተ ልማት ላይ ያተኮረ የልምድ ልውውጥ በማድረግ ከፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የኢንፎርሜሽን ሲስተም ሰርቪስ የዳታቤዝና ሶፍትዌር ልማት ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ አስቴር አለበል ጋር ተወያይተዋል፡፡
ስራ አስኪያጇ ወ/ሮ አስቴር የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት በኢንፎርሜሽን ሲስተም የደረሰበትን ደረጃና የሚሰጠውን አገልግሎት ለልዑካን ቡድኑ ሰፊ ገለፃ በማድረግ በአዲስ መልክ የተደራጀውን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዋና ኦዲተር መ/ቤትን አቅም ለመገንባት የሚያስችሉ የአይሲቲ መሰረተ ልማት፣ የአቅም ግንባታ፣ የአሠራር ሥርዓት እና መሰል ጉዳዮች ዙሪያ ገለጻ አድርገውላቸዋል፡፡
በመጨረሻም ከክልሉ ዋና ኦዲተር መ/ቤት የመጡት የልዑካን ቡድን አባላት ጉብኝቱ በቀጣይ ወደ ሥራ ለመግባት የሚያስችላቸውን ልምድና ጠቃሚ ተሞክሮ ያገኙበት መሆኑን ገልጸዋል፡፡