News

16ኛው የብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን ተከበረ

የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት፣ የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስና የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን አመራሮችና ሠራተኞች በተገኙበት 16ኛው የብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን ተከብሯል፡፡

ሶስቱ የፌዴራል ተቋማት በሚገኙበት ቅጥር ግቢ “የሰንደቅ ዓላማችን ከፍታ ለህብረ ብሔራዊ አንድነታችንና ሉዓላዊነታችን ዋስትና ነው” በሚል መሪ ቃል በተከናወነው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን አከባበር ሥነሥርዓት ላይ የፌዴራል ዋና ኦዲተር ክብርት ወ/ሮ መሠረት ዳምጤና ም/ዋና ኦዲተር ክቡር አቶ አበራ ታደሠን ጨምሮ የሶስቱ ተቋማት አመራሮችና ሠራተኞች እንዲሁም በአካባቢው የሚገኙ የፌዴራል ፖሊስ አባላትና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል፡፡

በኢትዮጵያ ህዝብ መዝሙር የታጀበው የሰንደቅ ዓላማ መስቀል ሥነስርዓት በፌዴራል ዋና ኦዲተር ክብርት ወ/ሮ መሰረት ዳምጤ የተከናወነ ሲሆን በስፍራው የተገኙ የፌዴራል ፖሊስ አባላት ሥነ ስርዓቱን በሰልፍ አጅበዋል፡፡

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *