News

መ/ቤቱ በተለያዩ የኦዲትና ኦዲት ነክ ጉዳዮች ዙሪያ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ሰጠ

የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ለኢ.ፌ.ዲ.ሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲቲዩት በተለያዩ የኦዲት፣ የግዥና የፋይናንስ አሠራሮች ዙሪያ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ሰጠ፡፡

ከነሀሴ 13 ቀን 2015 እስከ ነሀሴ 15 ቀን 2015 ዓ.ም በአዲስ አበባ በተሰጠው ስልጠና ከኢንስቲትዩቱ የፋይናንስ፣ የግዥ፣ የውስጥ ኦዲት እና ሌሎች ጉዳዩ ከሚመለከታቸው የስራ ክፍሎች የተውጣጡ የስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች መሳተፋቸው ታውቋል፡፡

ስልጠናውን የሰጡት የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት ኢንስትራክተር አቶ እዮብ ጉታ እንደገለጹት ስልጠናው በኦዲት ግኝቶች አስተያየት (Audit Recommendation)፣ በውስጥ ኦዲት (Internal Audit)፣ በኦዲት ግኝቶች (Audit Findings)፣ በፋይናንስና ግዥ (Finance & Procurement) እና ሌሎች ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ያተኮረ ነው፡፡

የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ለተለያዩ የፌዴራልና የክልል መንግስታዊ ተቋማት በኦዲትና ኦዲት ነክ ጉዳዮች ዙሪያ በርካታ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠናዎችን እየሰጠ ይገኛል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *