News

የግንባታ ኦዲት(Construction Audit) ላይ ያተኮረ ስልጠና ተሰጠ፡፡

ከተለያዩ የፋይናንሽያልና የክዋኔ ኦዲት ዳይሬክቶሬቶች ለተወጣጡ የኦዲት የስራ ኃላፊዎችና ከፍተኛ ኦዲተሮች በግንባታ ኦዲት (Construction Audit) ላይ ያተኮረ ስልጠና ተሰጠ፡፡

ስልጠናው ከሚያዚያ 3-18 /2015 ዓ.ም በስራ አመራር ኢንስቲቲዩት በሁለት ዙር የተሰጠ ሲሆን በጥቅሉ ከከፍተኛ ኦዲተርነት እስከ የኦዲት ዳይሬክተር ያሉ 195 የሚሆኑ ሰልጣኞች ተሳትፈዋል፡፡

ስልጠናው ለኦዲተሮች በግንባታ ግዥ ስርዓትና የውል አስተዳደር፣ በግንባታ ጥራት አጠባበቅ ሂደቶች እንዲሁም በግንባታ ኦዲት የስጋት ዳሰሳ ዙሪያ ግንዛቤን ያስጨበጠና በተሻለ አቅም ለመስራት የሚያስችል መሆኑን ከመ/ቤቱ የትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

የግንባታ ዘርፉ እጅግ እያደገና ውስብስብ እየሆነ እንደመምጣቱና ከፍተኛ በጀት የሚንቀሳቀስበት እንደመሆኑ ስልጠናው የተለያየ የልምድ ልውውጥ የተደረገበትና በዘርፉ ለሚደረግ የኦዲት ስራም ጠቃሚ ግብዓት የተገኘበት መሆኑን በስልጠናው ማጠናቀቂያ ላይ የገለጹት ሰልጣኞቹ በቀጣይም ተመሳሳይ ስልጠናዎችን የመስጠቱ ተግባር ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል፡፡

መ/ቤቱ ለስልጠናዎችና ግንዛቤ ማስጨበጫዎች ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት በየጊዜው በተለያዩ ዘርፎችና ደረጃዎች ለሚገኙ የመ/ቤቱ አመራሮችና ባለሙያዎች እንዲሁም ለባለድርሻ አካላት ጭምር ተከታታይ የሆኑ ተገቢ ስልጠናዎችን እየሰጠ ይገኛል፡፡

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *